ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ላደረጉት አስተዋጾ እውቅና ሊሰጣቸው ነው።የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስለ ሰብአዊ መብቶ…

https://cdn4.telesco.pe/file/Vm_lMrZGZrInT7-k3W7NqWUKNbjhRypAvc66MveMwyD_217w_ICF4z0D-O8egd4EiuPB3xvGwNawsGvEacYyEi07IGEfjYwCJC3CvqZIUCoz8WcU-jExLQDVyxYZiRhz3Z8wzuA26UWnJFnEHN1EHkn33FdITV-F1jsOj_eHsMe1D_Ayq4bk-6m-NzfYZgAU_p02K5z3H2P4mMC0r0zS20fWQVguLAA7aqmW50_ky0QRJ8c5ocYC1IAHxNnwPoaMv9nOLy29fPKWDVegPY5PMBvLWWA5XMQV7d2Vw_U2Y6gzA-KcqXQLG36Y-NLWTj8ydq602LzX6VMSTPYAvDpkvg.jpg

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ላደረጉት አስተዋጾ እውቅና ሊሰጣቸው ነው።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስለ ሰብአዊ መብቶች መከበርና የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን በመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ሊሰጣቸው ነው ብሏል።

የሰብአዊ መብቶች ቀን ከታህሳስ 1 ጀምሮ በኢትዮጵያ መከበር እንደሚጀምር ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ገልጿል።

አከባበሩም የተለያዩ ሁነቶች ያሉት እንደሆነ ታውቋል።

የሰብአዊ መብቶችን መጠየቅን ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ በርካታ የጉዳዩ ባለቤቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም በህይወት ዘመናቸው ላደረጉት የሰብአዊ መብት ተጋድሎ ነው ይህ እውቅና የሚሰጣቸው ተብሏል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply