ፖሊስ ተማሪ ቃልኪዳን ባህሩ አለመደፈሯን አረጋግጦ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት የህክምናው ሂደት ትክክል መሆኑን ማጣራት እና ማረጋገጥ ነበረበት ሲል የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አስታ…

ፖሊስ ተማሪ ቃልኪዳን ባህሩ አለመደፈሯን አረጋግጦ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት የህክምናው ሂደት ትክክል መሆኑን ማጣራት እና ማረጋገጥ ነበረበት ሲል የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አስታወቀ፡፡

በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ላይ በተፈጸመው አስገድዶ መድፈር፣ ዕገታና ፆታዊ ጥቃት ዙሪያ የወጡ የፖሊስ፣ የህክምና እና የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች እንደገና እንዲጣሩና ትክክለኛው መረጃ ለህዝብ እንዲደርስ ሲልም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር እና አጋሮቹ አስታውቀዋል፡፡

ቃልኪዳን ባህሩ የተባለች የ17 ዓመት ወጣት ላይ በቀን ጥቅምት 1/2014 ዓ/ም ከቤተሰቦቿ ጋር በምትኖርበት መኖሪያ ቤት፣ ተወስዳ መደፈሯ የተገለፀ ሲሆን፣
በድጋሚ ደግሞ በቀን መጋቢት 16/2016 ዓ.ም በማታውቃቸው ሰዎች ከምትኖርበት አካባቢ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዳ የአስገድዶ መድፈርና በባዕድ ነገር በማደንዘዝ እራሷን እንድትስት በማድረግ ጥቃት እንዳደረሱባት ተገልፆ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣን ያስነሳ ጉዳይ ሆነ ቆይቷል፡፡

ማህበራዊ ሚድያዎች የተበደለን ሰው በደል ከማውጣት እና አስፈላጊውን ምላሽ እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያና ድምፁ ያልተሰማ ሰው አገልግሎት ለማግኘት የሚረዳ ቢሆንም የማይገባን ጥቅም ለማግኘት፣
አሉባልታዎችን በመፍጠርና ተጠቂ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ሳያገናዝቡ የተዛቡ መረጃዎችን ማስተላለፍ አንዲት ጥቃት የደረሰባት ሴት መፍትሄ ወይም ፍትህ እንዳታገኝ እንቅፋት ይሆናል ሲል ማህበሩ ኮንኗል፡፡

ፖሊስ ተማሪ ቃልኪዳን ባህሩ አለመደፈሯን አረጋግጦ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት የህክምናው ሂደት ትክክል መሆኑን ማጣራት እና ማረጋገጥ ነበረበት ሲልም የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በመግለጫው ገልፃል፡፡

የፖሊስ ምርመራ መዝገቡ የተዘጋም ከሆነ ፋይሉ የተዘጋበትን ምክንያት፣ መዝገቡ የተዘጋው ለጊዜው ቢሆን እንኳን በቂ ማስረጃ ከተገኘ ሊከፈትና ምርመራው ሊካሄድ እንደሚችል ማስረዳት ሲገባው ይህንን ሳያደርግ በመቅረቱ በተጠቂዋ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም ችሏል ተብሏል፡፡

ፖሊስ መነሻውን የህክምና ሰነድ ብቻ በማድረግ በጉዳዩ ላይ በቂ ማስረጃ የለም ማለቱ፣ አጥቂዎችን ለመያዝ በቂ ክትትል አለማድረጉ እንዳሳዘነው ማህበሩ ገልፃል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር እና አጋር ድርጅቶቹ የሚመለከታቸው አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ሚኒሊክና ጴጥሮስ ሆስፒታሎች፣ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች፣ሚዲያ አካላትና መላው ህብረተሰብ ክፍል በጉዳዩ ላይ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ፖሊስ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ በሰራጨው መግለጫው አንዲት ወጣት እንደተደፈረች ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው ማለቱ አይዘነጋም፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply