ፖሊስ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀሙን ኢሰመኮ አስታወቀ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-c364-08db1c2519e3_tv_w800_h450.jpg

የዓድዋ ድል 127ኛ ዓመት በዓል ለማክበር አዲስ አበባ ምኒልክ አደባባይ በወጣው ሕዝብ ላይ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ከመጠን ያለፈ እርምጃ እስከሞት የደረሰ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።

የኢሰመኮ የሕግና ፖሊሲ ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት፣ “የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ከልክ ያለፈ እርምጃ ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን አረጋግጠናል” ብለዋል፡፡

ከትናንትናው ክስተት ጋር በተያያዘ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ “አንድ አባሌ ከመንግሥት ጸጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት ተገድሏል” ሲል፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም፣ “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ጊቢ አንድ ምእመን ሕይወታቸውን አጥተዋል” ብሏል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “የጸጥታ አካላት ሁለት ፈጣሪዎችን ለማስታገስ በሚያደርጉት ጥረት በቤተክርስቲያን በነበሩ ጥቂት ምዕመናን ላይ ጉዳት ደርሷል” ይታወቃል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply