ፖሊስ ከየትኛውም ሐይማኖት፣ ብሔር እና ፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዝኀነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም ነው አለ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፡፡የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሐይማኖቶች ብ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/uINO_sKy53uQqln-BorFZyD5xWHW1Nbs3dreZHqdIAqzkbs4sYk-uTyayN62XBOS2tDxXlJP4qmpii_4TYrgDkAUyVZtMlmzSmJnybautmMR99AIW0TSix2N4llcc_kTEf1dHHt40HubOIgDaStSVXr_LjheuDFs-hbCwfwvrT3Is7fQI2ROETXPIs5ntlMEVwlBwAI-cHW5vTZ1QFOXUlc8X6v7TSDF0q2bmAcqUtcFqhSzP-7Y98AozjP4wESRzsT0tEr9ntdMAnV5_6bPFHsROKtHgcN5yN48J48Dh31mW1TDKLpntAcHeZbDQIl3dLWJF9IrMMaFduyKtAdtSQ.jpg

ፖሊስ ከየትኛውም ሐይማኖት፣ ብሔር እና ፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዝኀነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም ነው አለ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሐይማኖቶች ብዝኀነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም እንደሆነ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ፤ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሐይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ የሚያሳየው በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን እየተሰራጨ ያለው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ሕግና አሠራር ውጭ እንደሆነ የፌደራል ፖሊስ አረጋግጧል።

አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ በመግለጫው አመላክቷል።

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply