ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ”ከህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ግንኙነት አላቸው” የሚል ክስ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ…

ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ”ከህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ግንኙነት አላቸው” የሚል ክስ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጳጉሜ 2/2014 በፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሃይሎች ተይዘው የተወሰዱት ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ ጳጉሜ 3/2014 ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ችሎቱ” የመዝገብ መደራረብ ገጠሞኛል” በሚል በይደር መዝገቡን ማሳደሩ ይታወሳል። ጳጉሜ 4/2014 በነበረው ችሎትም ፖሊስ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተብሎ የተፈረጀዉን የህወሀት የሽብር ቡድን በመደገፍ ከቡድን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተለያየ መንገድ በመገናኘት ተልዕኮ ተቀብለው ሲሰሩ ነበር የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል። መዓዛ መሃመድ የአማራ ክልል ህዝብ መንገድ ከፍቶ የህወሀት የሽብር ቡድኑን ማሳለፍ እንዳለበት እና ቡድኑ ወደ መሀል ሀገር ገብቶ ህገ-መንግስቱና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል መናድ እንዳለበት ፍላጎቷን ገልፃለች ሲል ፖሊስ ከሷል። ጎበዜ ሲሳይ ደግሞ “ጦርነቱ ሰልችቶናል ከፈለጉ አራት ኪሎ ሂደው ማፅዳት ይችላሉ የሚል ቀስቃሽ እና ሀገሪቱ ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር እንዲሁም የህወሀት ሽብር ቡድን ወደ መሀል ሀገር ገብቶ ንፁሀን ዜጎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ፣ንብረታቸውን እንዲያወድም ፣እንዲዘርፍ እና ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ እንዲያደርግ የተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገፆቸን በመጠቀምበማሰራጨት ላይ እያለ ተይዘል የሚል ክስ ቀርቦበታል። በዚህም ፖሊስ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ በሚል የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቋል። የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ይህንን የፖሊስን ክስና የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ጥያቄ ተቃውመው ተከራክረዋል። ጠበቃ አዲሱ የችሎቱን ሂደት አስመልክቶ ለሮሃ ቲቪ በሰጡት አስተያየት “ፖሊስ መዓዛ መሃመድን በዕስር ለማቆየት ስለፈለገ ነው እንጂ ከተባለው ጉዳይ ጋር የሚያገናኛት ነገር የለም ሲሉ” መካራከራቸውን ተናግረዋል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ጳጉሜ 4/2014 ከሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ሮሃ ሚዲያ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply