‹‹ፖሊ ጂሲኤል››የተባለው በነዳጅ ና ተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ የነበረው ኩባንያ ፍቃዱ ሊሰረዝ መሆኑን ሰምታናል፡፡ ኩባንያው አራት የፍለጋ እና አንድ የልማትና ምርት ፍቃድ ተሰጥቶት…

‹‹ፖሊ ጂሲኤል››የተባለው በነዳጅ ና ተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ የነበረው ኩባንያ ፍቃዱ ሊሰረዝ መሆኑን ሰምታናል፡፡

ኩባንያው አራት የፍለጋ እና አንድ የልማትና ምርት ፍቃድ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን፤ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በስራ ላይ የቆየ ቢሆንም የሚጠበቅበትን ስራ እንዳላከናወነ ተነግሯል፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር የ9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባቀረበበት ወቅት ፖሊ ጂሲኤል የተባለ የማዕድን ፈላጊ ኩባንያ ፍቃዱ ሊሰረዝ መሆኑን ገልጿል፡፡

የማዕድን ሚኒስቴሩ ታከለ ኡማ የሚጠበቅበትን ስራ ባለማከናወኑ ‹‹ተስፋ የተጣለበትን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት በተያዘለት ጊዜ ዕዉን እንዳይሆን እንቅፋት ፈጥሯል›› ብለዋል፡፡

“ይህ ኩባንያ ምን ሰራ ብለን እንዳንጠይቅ ምንም የሰራዉ ስራ የለም፤ ከሀገር ዉጡ እንዳንል ደግሞ ህግ ላይ የፈረመዉ ስምምነት ሀገርን እና ህዝብን የሚያስጠይቅ ነዉ “ያሉት ሚኒስቴሩ ፤
‹‹ከዓቃቤ ህግ ጋር ተነጋግረን ኩባንያዉ ከሀገር የሚወጣበትን ህጋዊ ሂደት እየተከተልን ነዉ ››ብለዋል፡፡

‹‹የጠየቅናቸዉን የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ዓቅም እስከ በጀት አመቱ ማጠናቀቂያ ማምጣት የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ፍቃዳቸዉን እንሰርዛለን›› ሲሉም አክለዉ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ኩባንያው የቻይና እንደመሆኑ ፤‹‹ከቻይና መንግስት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነና መንግስት ፈቃዱን ሲስጥ እውነተኛ የቻይና ኩባንያ ገብቶ እንዲያለማ እንጂ፣ የእኛ አፈር እና የእኛ  መሬት ላይ እንዲቀልድ አይደለም ፤ የሚቀልዱበት ዘመኑም አልፏል›› ሲሉ ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡ 

በተመሳሳይ ‹‹ኬፊ ሚኔራልስ›› የተባለ የወርቅ አምራች ኩባንያ ባለፉት 8 ዓመታት ዉል በገባዉ መሰረት የምርት ስራ ባለማከናወኑ ከየካቲት 2014 እስከ ሀምሌ 2014 ዓም ድረስ የፋይናንስ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ የመጨረሻ ማስጠን ቀቂያ እንደተሰጠዉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

እስከዳር ግርማ

ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply