ፖል ካጋሜ በቀጣይ ዓመት በምርጫ እንደሚወዳደሩ ተናገሩ፡፡የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለአራተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ተናገረዋል።ከፈረንጆቹ 1998 ጀምሮ ሩዋንዳን እሚመሩት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/m3vt-MlrcMAp8__HfEFEj7GGm3WnInmmhVU_bj8bMgQAElmSSOZWhypnCwZ4uCZ0IkXXd-T8sM1Eg0wJFaxv-3cc-MQwCewzl-he66buoZ9Sk6QnWOyFCzz3_qgOVl3ny3relRmsAPO6K3qoxUfCmwl5tnrj91NXGbnNS2clqiizPA-4uA_B4dUqoIuzWpanwXnwKP7GnIHJm3ho7SbS7R1B63UNNzEqnT8d1KyMSIV6T-PCb_JyVK00wTXhxzd3V85obSDk86BfPU6yJ8jwii6Crpioe6-yxtFfNENW6NAKteAKDCDLm7ORzNjXx2KA7gCCSYEqJDd5aDuFz6E0pQ.jpg

ፖል ካጋሜ በቀጣይ ዓመት በምርጫ እንደሚወዳደሩ ተናገሩ፡፡

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለአራተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ተናገረዋል።
ከፈረንጆቹ 1998 ጀምሮ ሩዋንዳን እሚመሩት ፕሬዝዳንት ካጋሜ ከዚህ በፊት ስልጣን እንደሚለቁ ተናግረው ነበር።

የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ በሚቀጥለው አመት በሚካሃደው ምርጫ በድጋሚ ለመወዳዳር እና ሩብ ክፍለዘመን ገደማ የሚሆነውን የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ሩዋንዳውያን በእኔ ላይ በሚያሳዩት መተማመን ደስተኛ ነኝ። እስከምችለው ድረስ ሁሌም አገለግላቸዋለሁ። በእርግጥም እጩ ነኝ” ብለዋል ካጋሜ።

ካጋሜ በነሐሴ 2017 በተካሄደው ምርጫ 98.63 በመቶ ድምጽ ለሰባት አመታት ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ካጋሜ ሀገሪቱን 800ሺ ሩዋንዳውያን ከተጨፈጨፉበት የ1994ቱ ዘርማጥፋት ወደ ሰላም እና ልማት በማሸጋገራቸው አለምአቀፍ አድናቆት አትርፈዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply