በቀጠናው እየተባባሰ የመጣዉን ግጭት ተከትሎ ፖፕ ፍራንሲስ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ጠይቀዋል፡፡
በጋዛ ለሰብዓዊ ዕርዳታ እና ድጋፍ የሚሆኑ ቦታዎች ሊከፈቱ እና ዜጎችም ከዛ የሚወጡበት መንገድ ሊመቻቸት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ፖፑ አክለዉም ሁለቱም አገራት ግጭቱን በማቆም የንጹሃንን ደም ማፍሰስ ማቆም አለባቸዉ ብለዋል፡፡
በግጭቱ ምክንያት ታፍነዉ የተወሰዱ እና የታገቱ ዜጎች እንዲለቀቁ ፤ህጻናት፣ አረጋዊያን እና ሴቶች እንዲሁም ሲቪሊያን ዜጎች በፍጹም የግጭቱ ሰለባ መሆን የለባቸዉም ሲሉ አበክረዉ ተናግረዋል፡፡
እባካችሁ ከዚህ በኋላ የንጹሃንን ደም አታፍስሱ ፣ በእስራኤልም፣ በዩክሬንም ሆነ በማንኛዉም ቦታ የሚደረጉ ጦርነቶች ይቁሙ፤ ጦርነት ሁሌም አክሳሪ ነዉ ብለዋል፡፡
በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል ግጭቱ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በሁለቱም ወገን የብዙ ንጹሃን፣ ህጻናት እና ጦርነት ዉስጥ ያልገቡ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
እስራኤል ለግጭቱ ምላሽ ወደ ጋዛ የሚሄድ የዉሃም ሆነ የመብራት መስመር አቅርቦትን በማቋረጧ ከ2007 ጀምሮ በከበባ ዉስጥ በሚገኘዉ በዚህ ሰርጥ የሚኖሩ ዜጎች ህይወት በእጅጉ ከባድ ሁኔታ ላይ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post