ፖፕ ፍራንሲስ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሃይሎችን ለማደራደር ደቡብ ሱዳን ሊያቀኑ ነው፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚጓዙት በሃገሪቱ የሰፈነውን ግጭት እንዲያበቃ ተፋላሚ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡
እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት ኑሯቸው አደጋ ላይ የወደቀውን ንጹሃን ዜጎች እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሆነ በደቡብ ሱዳን ሙላ በተሰኝችው ግዛት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ጳጳስ የሆኑት ስቴፈን አሜኑ ተናግረዋል፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ ወደ ደቡብ ሱዳን ለመምጣት የወሰኑት በፈረንጆቹ 2022 ቢሆንም በህመም ምክንያት ጉብኝታቸውን ማራዘማቸው አይዘነጋም፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ ደቡብ ሱዳን ከመድረሳቸው አስቀድሞ የእርሳቸው ከፍተኛ አማካሪዎች እና ጠባቂዎቻቸው ደቡብ ሱዳን ጁባ መድረሳቸውን ቢቢሲ አፍሪካ አስነብቧል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።