You are currently viewing ♦ በርግጥ ባለፉት 4 ዓመታት የሆነልን መልካም ነገር ከደረሰብን ክፉ ነገር ይበልጣል?!  ዶ/ር Dessalegn Chanie  1) በትህነግ የሽብር ወረራ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን…

♦ በርግጥ ባለፉት 4 ዓመታት የሆነልን መልካም ነገር ከደረሰብን ክፉ ነገር ይበልጣል?! ዶ/ር Dessalegn Chanie 1) በትህነግ የሽብር ወረራ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን…

♦ በርግጥ ባለፉት 4 ዓመታት የሆነልን መልካም ነገር ከደረሰብን ክፉ ነገር ይበልጣል?! ዶ/ር Dessalegn Chanie 1) በትህነግ የሽብር ወረራ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ክቡር ሕይዎታቸውን አጥተዋል። እነዚህ መሳውዕትነት የከፈሉ ዜጎች የሚወዷቸው ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች አላቸው። አገራችን በቅርብ ጊዜ ታሪኳ አይታው በማታውቀው መጠን የሰው ህይዎት ጠፍቷል፣ በትሪሊየን ብር የሚገመት ሀብት በጦርነት ወድሟል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችና ህፃናት በቡድን ተደፍረዋል፣ ለከፋ ስነ ልቡናዊ ጥቃት ተጋልጠዋል። በጦርነቱ መንግስት ተገዶ የገባበበት ቢሆንም የጠፋው የኢትዮጵያዊያን ህይዎት እንዴት እንደቀላል ይታያል? 2) ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ በሚሊየን የሚቆጠር ዜጋ ተፈናቅሏል፣ በቢሊየን የሚቆጠር ሀብት ንብረታቸው ተዘርፎና ወድሞ ዜጎች በአገራቸው አገር አልባ ተደርገዋል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ማንነት ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ተጨፍጭፈዋል፣ ህፃናት፣ እናቶች፣ አረጋዊያን በከንቱ ደማቸው ፈሷል። ይህንን የገዘፈ ችግርስ እንዴት ማሳነስ ይቻላል? ክቡርነትዎ፦ ከላይ የተገለጹት ችግሮች ብቻ ከተደረገልን የትኛው መልካም ነገር ጋር ይወዳደራሉ ? ህዝባችን እያለፈበት ያለውን መከራ አቃሎ በማቅረብ የሚገኘው የፖለቲካ ትርፍ ምንድን ነው? ፍዳውን ሲከፍል በከረመው ህዝብ ጫማ ውስጥ ሆኖ ጉዳዩን መመልከት ለምን ከበደን? አገራችን የገባችበትን ውስብስብ ችግር በመሸፋፈን የሚቃለል ችግር የለንም። ችግሩን መጋፈጥና መሰረታዊ የመዋቅር፣ የተቋማት እና የስሪት ማሻሻያዎችን ማድረግ፤ መንግስት ዋነኛ ሀላፊነቱ የሆነውን የህዝብና የአገር ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ላይ መስራት እንዳለበት ቢገልጹ ለእውነታው ይቀርቡ ነበር። © ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply