You are currently viewing ♦” በዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚመራው ኢሰመኮ  ለ500 አማራዎች ግድያ እና ከ20 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግድያ  ምክንያት ሁኗል ” ገነት አስማማው የአማራ ሚዲያ ማእከል  መስከረም 1…

♦” በዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚመራው ኢሰመኮ ለ500 አማራዎች ግድያ እና ከ20 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግድያ ምክንያት ሁኗል ” ገነት አስማማው የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 1…

♦” በዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚመራው ኢሰመኮ ለ500 አማራዎች ግድያ እና ከ20 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግድያ ምክንያት ሁኗል ” ገነት አስማማው የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 19 2015 አ/ም… አዲስ አበባ በምዕራብ ወለጋ ጃርዴጋ ጃርቴ የተጨፈጨፉት አማራዎች 500 ደርሷል። የወረዳው አመራሮች ጭምር የተሳተፉበት ይህ ኦፕሬሽን ካለ ጥፋታቸው ከ100 በላይ የታሰሩ አማራዎች በታሰሩበት እንዲቃጠሉ ተደርጓል ይህ ጭፍጨፋ እንዲፈፀም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ጳጉሜ ላይ ያወጣው መግለጫ immediate cause ሁኗል። ጉዳዩ እነሆ በዝርዝር👇 * ጳጉሜ ውስጥ የኢሰመኮ የጅማ ቅርንጫፍ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ የአማራ ኢ መደበኛ ታጣቂዎች ኦሮሞዎችን ገደሉ ብሎ መግለጫ አወጣ። ይኸው ሊንኩ👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1441128363030726&id=202584253551816 የኢሰመኮ የጅማ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ደቻሳ አለማየሁ ይባላል። ቀንደኛ የኦነግ ሸኔ ደጋፊ ነው። የፌስቡክ ገፁ ፕሮፋይል የኦነግ ነው። አሁን ፌስቡኩን ዲአክቲቬት አድርጎታል * የኢሰመኮ መግለጫ ከወጣ ከሁለት ቀን በሗላ የጃርቴ ወረዳ አመራሮች ጃርዴጋ የሚኖሩ አማሮችን ኦሮሞን እየገደላችሁ ነው ኢሰመኮ እንኳን ሽብርተኛ መሆኑን መስክሯል ብለው ከ100 በላይ አማራዎችን ጃርቴ ላይ አሰሯቸው(እነዚህ አማራዎች ትላንት እዛው እንደታሰሩ እንዲቃጠሉ ተደርጓል። ከ500ው ውስጥ አሉበት) * መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም የጃርቴ ወረዳ አመራሮች ወደ ጃርዴጋ ሒደው የአካባቢውን ህዝብ ይሰበስባሉ። አመራሮቹም ሰሞኑን ኦነግ ሸኔ የሚሰራው ኦፕሬሽን ስላለ የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ የሆናችሁ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ። የአካባቢው ሚሊሻ የሆናችሁ የአማራ ተወላጆች ደግሞ ትጥቃችሁን እንድትፈቱ ሲሉ ለተሰበሰበው ህዝብ ለፈፉ። የአማራ ተወላጆች እኛም አብረን እንውጣ እንሰደድ ሲሉ አመራሮቹ እኛ ስለ እናንተ አያገባንም ወደ የትም መውጫ የላችሁም ተከባችሗል ብለው ይመልሱላቸዋል። የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የአማራ ተወላጅ ሚሊሻዎችን በተባለው መሰረት ትጥቅ አስፈታ። ከዚያም *” ከመስከረም 10 አመሻሹን ጀምሮ እስከ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የኦሮሞ ተወላጆች በተባሉት መሰረት አካባቢውን ለቀው ወጡ። አብረው በጉርብትና የኖሩ ናቸው እና አይዟችሁ እሮብ ለሊት 11 ሰአት ላይ ኦነጎቹ እንደሚመጡ መረጃ ሰምተናል ተጠንቀቁ አይዟችሁ ብለው አማራዎችን አፅናንተው የኦሮሞ ተወላጆቹ በተባሉት መሰረት ከብቾቻቸውን ሳይቀር ይዘው ከአካባቢው በ12 ሁሉም ለቀው ወጡ * የኦሮሞ ተወላጆች ለአማራዎቹ በነገሯቸው መሰረት በዙሪያው ያለው ኦነግ አመሻሹን 11 ሰአት ጀምሮ አንዳንድ የተኩስ ድምፅ ማሰማት ጀመረ። አማራዎቹ ሚስት እና ልጆቻቸውም ወደ ጫካም ወደ በቆሎም ውስጥ ደብቀው የሚመጣውን ለመቀበል ተዘጋጁ። ኦነግ መስከረም 12 ረቡዕ ሌሊት 11 ሰአት ጀምሮ በጃርዴጋ ያሉትን አማራዎች መጨፍጨፍ ጀመረ። ከጃርዴጋ የዋይታ ጩኸት ቢሰማም የሚደርስ ጠፋ። የወረዳው አመራሮች ጋ ቢደወል እየሳቁ ምንም ማድረግ አንችልም ቻሉት የሚል የምፀት ምላሽ ተሰጠ። የዞኑ አመራሮችም ሲደወልላቸው ስልክ ዘጉ። ይህ ኦፕሬሽኝ ሲጀመር ግን ጃርዴጋ የሚኖሩ አማራዎች ለሚዲያ አካላት ሲወተውቱ ሰንብተው ነበር ሰሚ አላገኙም እንጂ። እኔ የነገሩኝን አድርሻለሁ። ድምፅ እንዲሆኗቸው ለፖለቲካ አመራሮች እና ፌስቡክ ላይ ተከታይ ላላቸው ግለሰቦች ድምፅ እንዲሆኗቸው ተናግሬ ነበር። ወደ ጉዳዩ ስመለስ👇 * ጃርዴጋ ላይ ንፁሀኑ መጨፍጨፋቸውን የሰሙ በሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ተተክተው ጃርቴ ወረዳ ላይ ያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተጨፍጫፊዎችን ለማዳን ወደ ጃርዴጋ ሲያቀኑ ወረዳው ላይ ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የፌደራል ፖሊስ አባላቱን ከሗላ ወግቶ ከ20 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ገደለ። የፌደራል ፖሊስ አባላት ይህ ጥቃት ሲፈፀምባቸው አካባቢውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። * የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ቅዳሜ ዕለት በሰጠው መግለጫ በጃርዴጋ ጃርቴ ኦነግ ሸኔ እና ኢመደበኛ ታጣቂዎች ሚሊሻዎችን እና ንፁሀንን ገደሉ የሚል የሀሰተኛ መግለጫ ሰጠ። ይህን የሀሰት መግለጫውን ሲያብራራም ኦነግ ሸኔ አዛዦቹ ስለተገደሉበት እና ህወሀትም እየተሸነፈች ስለመጣች የበቀል እርምጃ ለመውሰድ አስቦ ነው አልተሳካለትም፣ ቡድኑ አሁን ላይ እርምጃ ተወስዶበት እየተበታተነ ይገኛል ሲል ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጠ። የለገሰ ቱሉ መግለጫ ከእውነት የራቀ እና የንፁሀንን ጭፍጨፋ ለመሸፋፈን እንዲሁም መንግስታዊ መዋቅር ተዘርግቶለት የአማራን ጭፍጨፋ የሚያስፈፅመውን ማፊያ ቡድን በደም የተነከረ ወንጀሉን ለመሸፉፈን የሔደበት ርቀት ነው። * የለገሰ ቱሉን መግለጫ ተከትሎ የኢሰመኮ የጅማ ቅርንጫፍ ሌላ የክህደት መግለጫ አወጣ። የአማራ ኢ መደበኛ ታጣቂዎች ንፁሀንን ገደሉ የሚል መግለጫ አውጥቶ በኢሰመኮ ገፅ ተለቀቀ👇 ፅንፈኛ የኦነግ ሚዲያዎች የጃዋር መሐመድ ሚዲያን ጨምሮ ሲያራግቡት ሰንብተዋል https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=396374209357327&id=100069542521688 * በጃርዴጋ ከመስከረም 12 ቀን 2015ዓ.ም. የጀመረው ጭፍጨፋ እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ እየተካሔ ነው። የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ወደ አካባቢው ሒዷል ነገር ግን ከኦነግ ጋር አብሮ እየጨፈጨፈ ያለው አማራዎችን ነው። ጃርቴ ላይ ምንም ሳያጠፉ የታሰሩ ከ100 በላይ አማራዎች እንዲቃጠሉ ተደርጓል በርካታ ህፃናትን ጨምሮ ሴቶች በአጠቃላይ ንፁሀን ተጨፍጭፈዋል 2015 ዓ.ም ከመስከረም 12 ቀን ሌሊት አመሻሹ ላይ ተጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ የቀጠለው የጃርዴጋው ጭፍጨፋ ያልተቆጠሩትን አስከሬናቸው የጠፋው እና ጅብ የበላው ሳይቆጠር 500 ደርሷል። የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ይህ ሁሉ ኦፕሬሽን እና ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ባለበት ወቅት በኢትዮ ቴሌኮም ተባባሪነት የስልክ አገልግሎት ዘግተው ነው ጭፍጨፋው እየተፈፀመ ያለው ይህንን ጭፍጨፋ አትናገሩ ዝም በሉ የሚሉ ጥቁር አማራዎችንም እያየሁ ነው ዶክተር ዳንኤል በቀለ የጅማ ቅርንጫፍ ሰራተኞቻቸውን ማንነት ካወቁ በሗላ ይቅርታ የሚጠይቁ ይመስለኛል። አሁን ላይ ዶክተር ዳንኤል ኢትዮጵያ ውስጥ የሉም ሼር አድርጉት

Source: Link to the Post

Leave a Reply