
⚫️#አርበኛ_ዘመነ_ካሴ በወቅታዊ ጉዳይ ከወህኒ ቤት መልዕክት አስተላልፏል ⚫️ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ”ለመኖር ለመከራም ስንል በፍርሃት ወይ በስንፍና ወይም ባለማወቅ አስር ጠላት ስንለማመጥ አንዱ ድንገት ይክደናል። ትምህርት ሳንወስድ ዘጠኙን መለማመጥ እንቀጥላለን። (ነፃነትን ተናንቀህ ማጅራት መተህ እንጂ ጎዳና ላይ ጨርቅ አንጥፈህ ለምነህ ታገኘው ይመስል) ሌላኛውም ብድግ ብሎ ይክድሀል። አሁንም ስምንቱን መለማመጥ እና ጀርባቸውን ማሸት እንቀጥላለን …… ተራ በተራ ከድተውን ከድተውን ብቻችንን እስክንቀር ልምምጣችን እና ሳይመጥን መሳቃችን ይቀጥላል። በመጨረሻም አስሩም በአንድ ሆነው ግንባር ፈጥረው ሊያጠፉን ሲመጡ እኛ ብቻችንን ግን ተነጣጥለን ቆመን ያገኙናል። አስርን ጠላት አስር ሆኖ ተበታትኖ ቆሞ ማሸነፍ አይቻልም በፍፁም ፅኑ አንድነት እንጂ። አንድ እንሁን። አንድነት አንድነት አንድነት….. #አንድ_ሲኖዶስ ⚫️ #አንድ_ፓትርያርክ ⚫️ #አንድ_ቤተክርስቲያን⚫️ #ድል_ለአማራ_ህዝብ ⚫️ #ድል_ለኢትዮጵያ_ህዝብ ⚫️ {አርበኛ ዘመነ ካሴ ባውቄ ከባህርዳር ወህኒ ቤት} ለሶስና ፈቃዱ (ሶሲ) ጽናት ሚዲያ🖤🖤🖤 “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post