You are currently viewing ✍️መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የተፈፀመው ጭፍጨፋ ዘርን መሰረት ያደረገ እንደነበር ተገለፀ‼   ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እራሱን የጉምዝ ነፃ አውጭነኝ በሚል  የሚጠራ…

✍️መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የተፈፀመው ጭፍጨፋ ዘርን መሰረት ያደረገ እንደነበር ተገለፀ‼ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እራሱን የጉምዝ ነፃ አውጭነኝ በሚል የሚጠራ…

✍️መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የተፈፀመው ጭፍጨፋ ዘርን መሰረት ያደረገ እንደነበር ተገለፀ‼ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እራሱን የጉምዝ ነፃ አውጭነኝ በሚል የሚጠራው ሸፍታ ቡድን የብልፅግና መንግሥት ከጫካ አውጥቶ በጀት በመመደብ በግልገል በለስ ከተማ የከተማው ከፍተኛ ቦታላይ ካንፕ ሰርቶ በማስቀመጥ በአማራ ተወላጆች ላይ ብሄር ተኮር ጭፍጨፋ ተደርጓል። በመንግስት የሚደገፈው ይህ ታጣቂ ቡድን በግልገል በለስ ከተማ በትናንትናው እለት በርካታ አማራዎቸሰ ህፃናትን ጭምሮ ጨፍጭፏል ። ይህ የተደራጀ ሀይል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል እና በፌዴራል መንግሥት በበጀት የሚደገፍ መሆኑን ከውስጥ ምንጮች አረጋግጠናል ። በሰላም ስምምነት በሚል ከወራቶች በፊት ከሱዳን ደንበር ከነሙሉ ትጥቁ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ አሁን ላይ መንግሥት ፈቅዶ ሲያስገባው ለዚሁ አላማ እንደነበርም ጨምረው ገልፀውልናል። በቀን 30/10/2015 ዓም ለረጂም ሰዓት ያለማቋረጥ በግልገል በለስ ከተማ ተኩስ በመክፈት በአማራ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ የሞትና የአካል ጉዳት አድርሰዋል። # ጭፍጨፋውም የአማራ ተወላጆችን ያማከለ እንደነበር የመረጃ ምንጫችን ገልፀዋል። በትናትናው ዕለት የተጨፈጨፉት ዛሬው ዕለት በጂምላ ተቀብለዋል። በአሁኑ ሰዓት መከላከያ ሰራዊት በቦታው የደረሰ ቢሆንም ከታጠቀው ከገዳዩ የጉምዝ ሽፍታ ሀይል ጋር ያደረገው የተኩስ ልውውጥም ሆነ የወሰደው አርምጃ የለም ። ታጣቂ ቡድኑም ጭፍጨፋ ከፈፀሙ በኋላም ወደ ካምፓቸው ተመልሰዋል የተባለ ሲሆን፤ ካምፓቸው የከተማው መግቢያ ጫፍ ላይ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ አጠገብ እንደሚገኝ ተገልጿል። 👉👉# Share ይደረግ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply