You are currently viewing ✍️ በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት ድርቁ በሰው እና በእንስሳቱ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ተገለፀ። ✅ የካቲት፦…

✍️ በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት ድርቁ በሰው እና በእንስሳቱ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ተገለፀ። ✅ የካቲት፦…

✍️ በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት ድርቁ በሰው እና በእንስሳቱ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ተገለፀ። ✅ የካቲት፦ 26/2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ ) ✍️ በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት ድርቁ በሰው እና በእንስሳቱ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ተገልጿል። ✍️ በደቡብ ኦሞ ዞን ስር የምትገኘው ሐመር ወረዳ እንደ ሶማሌ እና እንደ ቦረና ሁሉ ለወረዳችን ለአርብቶ አደሮች ጊዜው ከፍቷል። በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት የአርብቶ አደሩ የኑሮ መሠረት የሆኑት የቀንድ ከብቶቹ በየጫካና ጥሻዎቹ ውስጥ በተኙበት እየሞቱ ነው። ሰውነታቸው ፈርሶ አጥንታቸው ገጦ የወዳደቁ እንስሳት በድን እዚህም እዚያም ይታያል። ሞታቸው ትኩስ ለመሆኑ ሳይበሰብስ ተቦጫጭቆ በአጥንታቸው ላይ የቀረ ቆዳቸው ይመሰክራል። ✍️ “አሁን ላይ በሐመር ድርቁ ዕለት በዕለት የአርብቶ አደሩ መተዳደሪያ የሆኑ የቁም እንስሳትን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨረሰ ነው። ውኃ የለም፤ ሣር የለም። አርብቶ አደሩ የእንስሳት ተዋጽዖ በመመገብ ነው የሚኖረው። ዝናብ የለም በዚህ ምክንያት ብዙ ከብቶች እየሞቱ ነው። ሰውም በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በረሐብ እየተሰቃየ መሆኑን ከወረዳ የተውጣጣው የምግብ ዋስትናና የአደጋ መከላከ ግብረኃይል መመልከት ተችሏል። ✍️ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ፎራ ጋርሾ እንዳሉት በወረዳችን ለተከታታይ አራት ዓመት በላይ በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ነው ይኸ [ድርቅ] በከፍተኛ ኹኔታ የተፈጠረው ያሉ ሲሆን ዝናብ በሚጥልበት ጊዜ አርብቶ አደሩ ኩሬዎች እና ወራጅ ውኃዎችን ነው የሚጠቀመው በማለት አሁን ላይ ግን እነዚያ ሙሉ በሙሉ ደርቀዋል፤ ጠፍተዋል” ሲሉ ተናግረዋል። አርብቶ አደሩ የግጦሽ አማራጮችን ለመፈለግ ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንስሳቱን በሚያንቀሳቅስበት ወቅትም አላስፈላጊ ግጭቶች እንደሚፈጠሩ አብራርተዋል። የእንስሳት መኖ አለመኖሩ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። በየትኛውም አማራጭ ውኃ ማግኘት ወደማይቻልበት ሁኔታ ነው የተደረሰው” ሲሉ የችግሩን ብርታት አቶ ፎራ ጋርሾ በሰፊው አብራርተዋል። ✍️ በመቀጠልም በወረዳችን ለ4ት አመታት በላይ በቂ ዝናብ ባለመዝነቡ እንስሳቱ የሚግጠው ሳር መጥፋቱ የወንዞች መድረቅ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቀንድ ከብቶች ለሰው ልጅ የመጠጥ ውሃ የተቆፈሩ የጉድጓድ ውሃዎችን ፖምፕ እየተደረጉ ለማጠጣት ቢሞከርም ከአቅም በላይ በመሆኑ የከርሰምድር ውሃ አየሸሸ መሄዱና የፓምፖች ብልሽት በየቀበሌው እየተከሰተ መሆኑን ገልፀው በሰው ላይ ከዚህ የከፋ ችግር ከመከሰቱ በፊት መንግስትና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቦዋል። ✍️ የሐመር ወረዳ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጥላሁን ባደገ እንደገለፁት በአሁን ወቅት የሚታየው ድርቅ በአንድ ግዜ የተከሰተ ሳይሆን ላለፉት ዓመታት የዝናብ እጥረት ውጤት መሆኑና የዘንድሮውን የተለየ የሚያደርገው ከወዲሁ በርካታ ቁጥር ያለው እንስሳት መሞት መጀመሩ ሲሆን በአሁን ግዜ የእንስሳት መኖ፣ ለሰው ልጅና ለእንስሳት የሚሆን የመጠጥ ውሃ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ መኖሩን ገልጸዋል። በመቀጠልም ላለፉት ዓመታት የሰብል ምርት አለመኖር በአከባቢው ከፍተኛ የምግብ እህል እጥረት ያስከተለ ሲሆን በዚህም እናቶችና ህፃናት እንዲሁም አረጋዊያን የችግሩ የመጀመሪያ ተጠቂ ሆነዋል። ✍️ ይህ የሚስተዋለው ደረቃማ የአየር ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ በአከባቢው በሰውና በእንስሳቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ስጋታቸውን የገለፁ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሁሉም አካላት በተቀናጀ መልኩ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ✍️ የአርብቶ አደሩ እንስሳትም ሞት የበረታው በሐመር ወረዳና ቱርማ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በ38ቱም ቀበሌዎች ውስጥ መሆኑን ተገልጿል። ✍️ የግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ሼላ እንደገለፁት የአርብቶ አደሩን የምግብ ዋስትና በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ በወረዳ ደረጃ የወይጦ ወንዝን በመተማመን ሠፊ ጥረቶች ተደርገው በኤርቦሬ ጓንዶሮባ፣ ጨርቀቃና ዘገርማ በርካታ የጓሮ አትክልቶችን እንደሙዝና የመሳሰሉትን ተተክለው ፍሬ በመስጠት ላይ ሳሉ የወይጦ ወንዝ ሙሉ በሙሉ በመድረቁ ምርት ሊሰጡ የደረሱ ሙዞችና በአስሌ ሬቦ መንደር በዘር ተሸፍኖ የበቀለው የቆላ ስንዴ ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልፀዋል ✍️ በሕይወት የቀሩት የቤት እንስሳትም ቢሆኑ ሰውነታቸው አልቆ አጥንታቸው ቆዳቸውን እየገፋ ነው። በየጥሻው የቀሩ የቤት እንስሳት የሐመር አርብቶ አደር የኑሮ መሠረት ነበሩ። ውኃ የጠማቸው፣ መኖ የቸገራቸው የቀንድ ከብቶች በኦሞ ሸለቆ ለሚኖረው አርብቶ አደር ብቸኛ ጥሪት ናቸው። ✍️ በድርቁ ሰለባ የሆኑት አርብቶ አደሮችም መንግስት እንስሳቱን “የሚታደግ እርዳታ” እንዲያቀርብላቸውና “ቀሪዎቹ እንስሳት ተርፈውልን እኛም ከእነሱ የሆነ ነገር እያገኘን ራሳችንን የምናተርፍበት ሁኔታ ቢፈጠር በማለት አሁን ሣር የለም፤ ግጦሽ ማግኘት አይችሉም። ይኸንን መነሻ አድርገው መኖ የሚቀርብበት መንገድ እዲመቻችላቸው፤ ውኃ እንዲደርስላቸው፤ እንስሳት ቢሞቱ እንኳን የሰው ልጅ ውኃ የሚያገኝበት ሁኔታ ቢመቻችልን” በማለት አቤቱታቸውን ለመንግስት አቅርበዋል። ✍️ መረጃውን Share በማድረግ የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ። ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው ❗❗ መረጃውን ያደረሰን የሐመር ወረዳ ኮምኒኬሽን ነው ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply