You are currently viewing ❝መዝመት፣ አካባቢን ነቅቶ መጠበቅ፣ ጸጉረ ልውጦችን መከታተል እና ለወገን ጦር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል በአጭር ጊዜ ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይልን ማጥፋት ይገባል❞ ብርጋዴ…

❝መዝመት፣ አካባቢን ነቅቶ መጠበቅ፣ ጸጉረ ልውጦችን መከታተል እና ለወገን ጦር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል በአጭር ጊዜ ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይልን ማጥፋት ይገባል❞ ብርጋዴ…

❝መዝመት፣ አካባቢን ነቅቶ መጠበቅ፣ ጸጉረ ልውጦችን መከታተል እና ለወገን ጦር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል በአጭር ጊዜ ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይልን ማጥፋት ይገባል❞ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አብሮ ኖሮ መራራቅን እና ጥላቻን፣ በተደረገለት በጎ ነገር ፋንታ ክፋት እና ሴራን ገና ከምስረታው ጀምሮ የለመደው ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ በኢትዮጵያ እና በአማራ ሕዝብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ አሳልፏል፡፡ በመከራዋ ደስታውን፣ በድህነቷ ሃብቱን እና በጉስቁልናዋ ጉልበቱን ሲያበረታ የነበረው ይህ ኃይል ከሥልጣን በተወገደ ማግስትም እንደለመደው ሁሉ የእናት ጡት ነካሽነቱን ቀጥሎበታል፡፡ ልክ የዛሬ አንድ ዓመት የትግራይን ሕዝብ እና ኢትዮጵያን በቀበሮ ዋሻ ውስጥ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሲጠብቅ የኖረውን፣ የትግራይ እናቶችን መኖሪያ ቤት የሠራውን፣ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሕጻናትን ያስተማረውን እና በሰላም ጊዜ ገበሬ ሆኖ የኖረውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጀርባ በመውጋት የክህደት ጥጉን ለዓለም ሕዝብ አመላከተ፡፡ በወቅቱ መንግሥት በሽብር ቡድኑ ላይ በወሰደው ጠንካራ እና ፈጣን ምት ምድር አይብቃን ያሉት ኃይሎች የሞተው ሞቶ፣ የታሰረው ታስሮ ቀሪዎቹ በየጢሻው እና በየጉድጓዱ እንዲቀረቀሩ ሆነ፡፡ አሸባሪው ኃይል በከፈተው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ለዓመት ያክል ሳይዘራ እና ሳይሠራ ከርሟል በሚል እና ጎጂና ጠቃሚውን ለይቶ እንዲወስን መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ ኅላፊነት ተሰምቶት የማያውቀው እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ደምና ላብ የቅንጦት ኑሮውን የኖረው ሽብርተኛው እና ዘራፊው የትግራይ ወራሪ ኃይል የተኩስ አቁም ውሳኔውን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስዶ በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ በመፈጸም ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ውድመቶችን ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ይገኛል፡፡ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል የተራዘመ የወረራ ሂደትን በመምረጥ የአማራ ሕዝብን ሁለንተናዊ ጉስቁልና ማየት ቢናፍቅም ይህንን የተረዳው የክልሉ መንግሥት ለሕዝቡ የክተት ዘመቻ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የክተት ጥሪው ምላሽ እና የሽብር ቡድኑ ጥፋት ምን መልክ አለው? ሲል የአማራ ልዩ ኅይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን አነጋግሯል፡፡ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በቀቢጸ ተስፋ በአማራ እና በአፋር ሕዝብ ላይ በከፈተው ወረራ በገባበት መንገድ መውጣት እንደማይቻል አውቋል ነው ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፡፡ አሸባሪው ኃይል በተስፋ መቁረጥ እየወሰዳቸው ያሉት ርምጃዎች ይህንን አመላካች መሆናቸውን በመጥቀስ፡፡ አሸባሪው ኃይል ድጋሜ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕልውና ሥጋት በማይሆንበት ደረጃ ማጥፋት የግድ መሆኑንም ነው የልዩ ኃይል አዛዡ የገለጹት፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን እንቅስቃሴ ለመግታት እና የወረራቸውን አካባቢዎች ነፃ ለማውጣት ከመደበኛ ሠራዊቱ በተጨማሪ ሕዝባዊ ማዕበል ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ለዚህም ሲባል የክልሉ መንግሥት የክተት ጥሪ አስተላልፏል ነው ያሉት፡፡ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ❝ዛሬ የተረከብናትን እና የምንኖርባትን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የነፃነት ማማ ክብር ያገኘናት ያለ ዋጋ አይደለም❞ ብለዋል፡፡ የአሁኑ ትውልድ በተለይም ወጣቱ የአባቶቹን ውርስ ማስጠበቅ እንደሚኖርበት በማሳሰብ፡፡ ❝መዝመት፣ አካባቢን ነቅቶ መጠበቅ፣ ጸጉረ ልውጦችን በመከታተል እና ለወገን ጦር ሁሉን አቀፍ ድጋፍን አጠናክሮ በመቀጠል በአጭር ጊዜ ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ኃይልን ማጥፋት ይገባል❞ ነው ያሉት፡፡ በክተት ጥሪው መሠረት የሥራ ኀላፊዎች እና ሕዝቡ ተናበው እየሠሩ ነው፤ ወራሪ ኃይሉን መቅበር እንጂ መመለስ አይገባምም ብለዋል፡፡ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል የያዘው ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ እና ውድመት የሚመከተው በተናበበ ሕዝባዊ ማዕበል መሆኑንም ገልጸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply