You are currently viewing ❝የህልውናችን ማስከበሪያ ቀዳሚው ጋሻና ጦራችን የጸና አንድነታችን ብቻ ነው❞ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ  ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም /አሻራ ሚዲያ / የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ…

❝የህልውናችን ማስከበሪያ ቀዳሚው ጋሻና ጦራችን የጸና አንድነታችን ብቻ ነው❞ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም /አሻራ ሚዲያ / የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ…

❝የህልውናችን ማስከበሪያ ቀዳሚው ጋሻና ጦራችን የጸና አንድነታችን ብቻ ነው❞ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም /አሻራ ሚዲያ / የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ❝የህልውናችን ማስከበሪያ ቀዳሚው ጋሻና ጦራችን የጸና አንድነታችን ብቻ ነው❞ ብለዋል። አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ያስተላለፉት መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:- ለጠላት እንቶፈንቶ ጆሮአችንን ሳንሰጥ በጠላት ላይ ድልን ለመቀዳጀት ከምንጊዜውም በላይ እንትጋ። በአረጀና ባፈጀ አስተሳሰቡ ሀገርን ለማጥፋት ላይ ታች የሚለውና በሐሰት ድቡሽት ላይ የበቀለው አሸባሪው ትህነግ ጥርሱን በነቀለበት ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ዛሬም ሕዝብን የሚያዘናጋ ይመስለዋል። ስለሆነም ሕዝብን ለማደናገር ተሞክሮ የከሸፈውን ስልት ሲጠቀም ይስተዋላል። ኾኖም ግን በጠላት ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ የሚደናገር ሕዝብ እንደሌለን በተደጋጋሚ አሳይተናል። አሁንም የጠላት እንቶ ፈንቶ ላይ ሳይኾን የሕዝባችን አቅም ላይ ተመስርተን ግባችን የኾነውን ህልውናችንን የማስጠበቅ ሥራ በተሟላ አቅም ለመፈጸም መረባረብ ይኖርብናል። ድል የሚገኘው በተሰማራንበት ኹሉ በሚኖረን የራስ አቅምና ለሀገር፣ ለወገንና ለነጻነት ባለን ፍጹም እምነትና ተጋድሎ ነው። ለአሸባሪው ቡድን የሚንበረከክ፤ ክብሩን ዝቅ የሚያደርግና ለትውልዱ የውርደትን ታሪክ የሚያስረክብ አማራ ዛሬም ኾነ ወደፊት የለም፤ሊኖርም አይችልም። ይህንን የተረዳውና የአማራ ሕዝብ አንድነትና አሸናፊነት ከብረት የጠነከረበት አሸባሪው ቡድን በዋግኽምራ፣ በሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ወሎና በሰሜን ጎንደር (የተወሰኑ አከባቢዎች) ወረራ ፈፅሞ ሲያበቃ ንጹሐንን እየገደለ፣ የሕዝብና የመንግሥትን ንብረት እየዘረፈ ሕዝብን በማሰቃየት ጠላትነቱን እያሳየ “መንግሥት ትቷችኋል፤ አቅም የለውም፤ ይህንና ያን ሀገር ተቆጣጥሪያለሁ” በማለት ሕዝብን ከወረራ ነጻ ለማውጣት የሚዋደቀውን ሠራዊትና መንግሥት ይተቻል። ሕዝብንም ለማታለል ይሞክራል፡፡ ይህ ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ አንድም የአማራ ሕዝብ አንድነትን ለመበተን፤ አንድም ሕዝብ ከመንግሥት ጋር አንድ ልብ ኾኖ መቆሙ ፈተና ስለሆነበት ከገባበት ቅርቃር ለመውጣት የሚያደርገው መጋጋጥ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው። የወገናችን ህልውናና የሀገር ደኅንነት ተጠብቆ የሚኖረው ጠላትን በየተሰማራንበት ከመታገል በተጨማሪ በህይወት መኖርና ነፃነትን ከፈለግን ለመሞትም በመዘጋጀት ጭምር ነው። ምክንያቱም ያለመስዋእትነት የሚገኝ ድል የለምና። ስለሆነም ሕዝባችን ሙሉ አቅሙንና ትኩረቱን ጠላትን መፈናፈኛ በማሳጣት እንዳይወጣ አድርጎ መቅበሩ ላይ መሆን አለበት። ጠላትን ለመፋለም የሚያስፈልገው ትጥቅና ስንቅ ብቻ ሳይሆን የተሟላ አስተሳሰብ መሆኑንም በመረዳት እንደ እስካሁኑ ዛሬም ደማቅ ታሪክ ለመጻፍ በየተሰለፍንበት የጦር ግንባር በእጃችን ባለው የትኛውም አይነት መታገያ መሳሪያ ጠላትን ያለረፍት መፋለም የማሸነፊያ መንገዳችን ነው። በራችን ድረስ ሊያጠፋን የመጣን የጠላት ኃይል በደጃችን ከመቅበር ውጭ ሌላ ምርጫ የለንም። እንደ አማራ ሕዝብ ባህሪውን ጠንቅቀን የምናውቀው አሸባሪው ትህነግ ከፍጥረቱ ጀምሮ የአማራን ሕዝብ ለማጥፋትና ኢትዮጵያንም ለማውደም የተፈጠረና ለዚህም ሲሠራ የኖረ መሆኑ ለደቂቃም አንዘነጋውም። ዛሬም ከዝገቱ የማይታደሰው ይህ ቡድን የአማራን ሕዝብ ደምና አንጡራ ሀብቱን እንደመዥገር ተጣብቆ እየተጣባና እየዘረፈ የመጨረሻ እስትንፋሱን ለማቆየት በመወራጨት ላይ የሚገኝ በመሆኑ የሚያናፍሳቸውን አሉባልታዎች ኹሉ ጠንቅቀን ልንረዳ ይገባል። ስለሆነም ጥንተ ተፈጥሮውንና አሁናዊ ባህሪውን አጥርተን የምናውቀው ጠላትን በመቅበር ላይ እንጂ በማደናገሪያ እንቶ ፈንቶው ሳንዘናጋ ትኩረታችን ትግሉን በሚደግፉ ጉዳዮቻችን ላይ እናድርግ። አልጋ በአልጋ የሚገኝ ድል የሌለ መሆኑን በመረዳት በትግሉ ሂደት የሚያጋጥሙ ክፍተቶች ካሉ እያረምን፣ እንቅፋቶችን እየጠረግን ለዓላማችን በፅናት እንፋለም!! በአሁኑ ሰዓት የህልውና ትግላችንን የሚያራክስና የጠላት አጀንዳዎችን ተቀብሎ የሚያራግብ ራሱ የአሸባሪው ቡድን አባል አልያም ደግሞ ተከፋይ ባንዳ ለመሆኑ ጥርጥር የለንም። እናም ከጠላት ፕሮፖጋንዳና ይህንኑ የጠላት ፕሮፓጋንዳ እንደ “ፓሮት” የሚያስተጋቡና የሚደጋግሙ ግለሰቦች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል። መረጃ ለሕዝብ ያደረሱ እየመሰላቸውና እያስመሰሉ የተከታይን ቁጥር ለማብዛት አልያም የዩቱዩብ ገንዘብ ለማፈስ በሚል ርካሽ ሐሳብ አክሳሪ ቁማር ውስጥ ባለመሰለፍ የሕዝባችንን ሥነ ልቦና እንጠብቅ። ሰለሆነም ተገቢ ያልሆኑ አቅማችንን የሚበታትኑ መረጃዎችን ባለመልቀቅ ለትግላችን አዎንታዊ ሚና ማበርከት ከሁላችንም ይጠበቃል። ስለሆነም ኃይላችንን አሰባስበን፤ አንድነታችንን አጠናክረን ሕዝባችን ላይ የተቃጣብንን አደጋ ለመቀልበስ መረባረብ የኹላችንም ግዴታ መሆን አለበት። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ለጠላት የሚዝል አማራ የትም አይኖርም። ኹሉም ትኩረቱንና የበረታ ክንዱን በየተሰማራበት የትግል ተልእኮ ላይ ያሳርፍ። ድል ለእውነትና ለፍትሕ ታጋይ ጀግኖቻችን!!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply