🌿ወደ የት ልጣራ🌿 ማን ነው አቤት የሚል ወደ የት ልጣራ፣ ከሰው በታች ሆነ ተደፈረ አማራ፣ ስለመጭው ነገር እኔስ ሆደ ፈራ። የደረስንበቱ ምነው ጊዜው ከፋ፣ እኛ እየተጣራን አቤት የሚል ጠ…

🌿ወደ የት ልጣራ🌿 ማን ነው አቤት የሚል ወደ የት ልጣራ፣ ከሰው በታች ሆነ ተደፈረ አማራ፣ ስለመጭው ነገር እኔስ ሆደ ፈራ። የደረስንበቱ ምነው ጊዜው ከፋ፣ እኛ እየተጣራን አቤት የሚል ጠፋ፣ በግፍ ተገደለ የሰው ደም ተደፋ፣ ቀብር አልደርስ ብሎ ሁኖ በወረፋ። አቤት በለኝ መንግስት ወዴት ነው ያለኸው፣ የአማራን ህዝብ ነገር ወዴት አደረስኩው፣ በጅምላ ሲገደል ምነው እረሳኸው፣ ሀብትና ንብረቱን ወንበዴ ሲዘርፈው። የሚሰማኝ አጣሁ ወደ የት ልጣራ፣ አማራን አረዱት እደበግ በካራ፣ አለቀ ህዝባችን ሁሉም በየተራ። መንግስትን ላላገኝ በከንቱ እየደከምኩ፣ አቤት የሚል ባጣ እኔም ተስፋ ቆረጥኩ፣ በዚች ከንቱ ምድር ለይስሙላ እየኖርኩ፣ ሀብት ንብረቱ ቆርቶ እሬሳ እየቆጠርኩ። የአማራን ህዝብ ነገር አፍ ላውጣ ልናገር፣ ማንንም ሳልፈራ ሳልደነጋገር፣ እሬሳ አፍ አውጥቶ ከሞትኩ ላይናገር። ለእኛ የደገሱት አለ ብዙ ድግስ፣ ህዝብ የሚያጎሳቁል እምነት የሚያረክስ፣ መፍትሄ የጠፋለት ህዝብን የሚያስለቅስ። ህዝብ ለምን አይከፋው ለምን አያለቅስ፣ አለውህ የሚለው ሲያጣ የሚደርስ፣ የአማራ ህዝብ ገላ ሲወድቅ ያለልብስ፣ በአፍንጫው ተደፍቶ በደሙ ሲርስ። የበይ ተመልካች የሰው ደስታ አድማቂ፣ ለእራሳችን ሳንሆን ሌሎችን ጠባቂ፣ ዛሬ እየ ተበደል ከንቱ አለም ናፈቂ። አለ ብዙ ሴራ እኛ የማናውቀው፣ ያልተገለፀልን ምስጢሩ ምንድን ነው፣ አማራ ተመርጦ ይጥፋ ያለ ማነው፣ ዝም አንበል ጎበዝ መታገል አሁነው። በአገራዊ ምርጫው ህዝብ የመረጣችሁ፣ ጠቅላይ ሚኒስትርሩ ስልጣን የሰጣችሁ፣ ምንድን አቀዳችሁ ምን እንስራ አላችሁ፣ በአማራ ጉዳይ ላይ ምንድን መከራችሁ፣ ልትታደጉን ነው ወይስ ይጥፉ አላችሁ? © ብዙዓየሁ ደስታ

Source: Link to the Post

Leave a Reply