
🔥«መከላከያ ሰራዊት ራያና ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት መደላድል እየሰራ ነው‼️» ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ህገወጥ ወታደራዊ አገዛዝ በአስቸኳይ ይቁም! ▪1. መከላከያ ሠራዊቱ በአማራ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ወረራ ከማካሄድ አልፎ ፣ የክልሉን አስተዳደራዊ መዋቅር በመንጠቅ ወታደራዊ አገዛዝ እንደመሠረተና ራያና ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት መደላድል እየሰራ እንደሆነ በግልፅ ሰምተናል። ሠራዊቱ በዚህ ደረጃ የአንድ ወገን የጥፋት አጀንዳ አራማጅና ጋሻ ጃግሬ መሆኑ ለአማራ ብቻ ሳይሆን ለመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እጅግ አስነዋሪ ንቀት ነው። ማናቸውም የወታደራዊ አገዛዝ አዝማሚያ በአስቸኳይ መታረም አለበት። ▪2. ከእንግዲህ መከላከያው በአማራ ክልል የሚያደርገው ህገወጥ እንቅስቃሴ በአማራ ህዝብ ላይ እንደተቃጣ ጠባጫሪነት ይቆጠራል። በመሆኑም ሠራዊቱ ሁለት የሰላምና የጦርነት ምርጫ አለው። አንደኛ በአስቸኳይ ከህገወጥ ስምሪቱ ታቅቦ በክብር ወደ ካምፑ መሰብሰብ ፤ በመደብ ከሚያስፈልገው መጠን የቀረው ሠራዊት ክልሉን በመልቀቅ ወደ ህጋዊ ግዳጁ መሰማራት አለበት። ሁለተኛ ሠራዊቱ የሰላም አማራጭን አሻፈረኝ ብሎ የኦህዴድና ወያኔን ሀገር የማፍረስ ሴራ በኃይል አስፈፅማለሁ ካለ በአማራ ህዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት እንዳወጀ ጠላት ይቆጠራል። በሀገርና በህዝብ ላይ ለሚፈፀመው ክህደት ተገቢው መስተንግዶ ይደረግለታል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post