
#ደራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሳዬ ደርቤ የፊታችን ዓርብ ሐምሌ 7ቀን 2015 ዓ.ም አቃቢ ህግ ክስ ለመመሥረት በጠየቀው መሠረት ፍርድ ቤት ይቀርባል‼ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አቃቤ ህግ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ባለው እና ፍርድ ቤቱ በፈቀደው መሠረት የሚቀጥለው አርብ 8 ሰአት የቀጠሮ ቀን ነው ። ደራሲ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የጠለስ ዩቱብ ሚዲያ መስራችና ባለቤት አሳዬ ደርቤ ሐምሌ 7/2015 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ጉዳዮች ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንደሚቀርብ አሻራ ሚዲያ ከጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ጋር በነበረው ቆይታ አረጋግጧል። ደራሲ አሳዬ ደርቤ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ አገዛዙ በላካቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ታፍኖ መወሰዱ አይዘነጋም። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post