1 ሽህ 495 ኛው የመውሊድ በዓል በማስመልከት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ባህርዳር //…

1 ሽህ 495 ኛው የመውሊድ በዓል በማስመልከት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር እድሪስ በዓሉን በማስመልከት ለእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 1 ሽህ 495ኛውን የመውሊድ በዓል በማስመልከት በሰጠው መግለጫ በዓሉ ሲከበር በመተሳሰብና መከባበር መሆን ይኖርበታል ብሏል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር እድሪስ በዓሉ ለአለም ፍጥረታት ሁሉ ሰላም የምንፀልይበት ነው ብለዋል፡፡ ሁሉም በዓሉን ሲያከብር እዝነት በተሞላበት መሆን ይኖርበታል ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር እድሪስ የነብዩ አስተምህሮና ተግባርም ይህን ስለማዘዝና ስለመተግበሩም አንስተዋል ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply