1.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበለው ግለሰብ እጅ ከፈንጅ መያዙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህ…

1.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበለው ግለሰብ እጅ ከፈንጅ መያዙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ 1.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበለው በገቢዎች ሚንስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት የኦዲት ዋና መሪ ባለሙያ እጅ ከፈንጅ ይዘውት ክስ መመስረቱን ገልጿል፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ በክሱ የወንጀል ዝርዝርም ተከሳሽ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ገቢዎች ሚንስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት የኦዲት ዋና መሪ ባለሞያ መላኩ ሸዋረጋ ቤኛ በስራ ኃላፊነቱና ማድረግ የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማግኘትና ለሌላ ሰውም ለማስገኘት በማሰብ ወንጀሉን መፈፀሙ ተመላክቷል፡፡ ግለሰቡ አንድ ድርጅት እ.ኤ.አ ከ2016 እስከ 2018 ላለው የግብር ዘመን የንግድ ስራ ትርፍ ግብር 66 ሚሊዮን 616ሺህ 818 ነጥብ 93 ሳንቲም እንዲከፍል በገቢዎች ሚንስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ሲወሰንበት የድርጅቱ የአስተዳደር ሰራተኛ በውሳኔው ላይ ለቅ/ጽ/ቤቱ ቅሬታ ሲያቀርብ ተከሳሹ አሰተዳደር ሰራተኛው ያቀረበውን ቅሬታ ውሳኔውን ዝቅተኛ በሆነ መልኩ መወሰንእንደሚቻል በመግለጽ 1 ሚሊዮን 500ሺህ እንዲከፍል መጠየቁ ተገልጿል፡፡ ተከሳሹ ከጠየቀው ገንዘብ ውስጥ ውስጥ ብር አንድ ሚሊዮን በባንክ ለመቀበል ቀሪውን ደግሞ በጥሬ ገንዘብ ለመቀበል በመደራደር ከተስማማ በኋላ በቀን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ካፒታል ሆቴል ውስጥ ብር 500,000 ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል መከሰሱን ተገልጿል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሙስና ወንጀል ችሎት በላከው የወንጀል ክስ ላይ ተከሳሽ መላኩ ሸዋረጋ ቤኛ ላይ በ2007 ዓ.ም በስራ ላይ የዋለውን የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 10 (2) ስር የተመለከተውን ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል በመተላለፍ በፈጸመው ወንጀል ክስ ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዘገባው የብስራት ሬድዮ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply