
አስራ አንድ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሶማሊያ ውስጥ ቦሳሶ አቅራቢያ በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ። የድርጅቱ የሶማሊያ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ይህ መኪና አደጋ የደረሰው ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 19/2015 ዓ.ም. ምሽት ላይ ሲሆን፣ ከሟቾቹ በተጨማሪ ቢያንስ 20 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። አደጋው የደረሰባቸው በባሕር በኩል ወደ የመን ለመሻገር የሚገዙ መሆናቸው ተነግሯል።
Source: Link to the Post