11 ኪሎ ግራም የሚመዝነዉ ድንች!ጂ2 ሆርቲካልቸር ፒ አል ሲ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት ይታወቃል፡፡ከሚያመርታቸዉ አትክልትና ፍራፍሬዎች መካከል ደግሞ የስኳር ድንች ይገኝበታል…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/bShFpUptABKYZomLFNBXh5qp3IO5CtNNzah6QF6FIeGPy3MiqyvK5oGSU45iwTT4F6ak1DA5J7rMYrvcrL1B-D2_7zd0OVH3yRNYNbU7c8ZlHdGO8ebrZWTJ4hfYNi4bhEMN-1LF2ReEVbQavTIIxhjoMYnn09B_6mjjzK-I7zmPMo--KSQTkW3XkuGPWpwNQu9Ho6f_l33PStgRWex6E92CGLtbxyRXsxL3cdiRUNUJhFiAU4dXg-UiAsQUbs7HNOW3rYrDhbaKA1N8VSZ-DCEdD5PGrkTjm2OXvQBR-hT8BMAuBDqF9QTZ5NqHfSmqGgPGohSd930aq77AjRci3A.jpg

11 ኪሎ ግራም የሚመዝነዉ ድንች!

ጂ2 ሆርቲካልቸር ፒ አል ሲ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት ይታወቃል፡፡
ከሚያመርታቸዉ አትክልትና ፍራፍሬዎች መካከል ደግሞ የስኳር ድንች ይገኝበታል፡፡

የጂ2 ሆርቲካልቸር ፒ አል ሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አንሳር ሮበሌ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ከእርሻ ማሳዉ ድንች በሚሰበስቡበት ወቅት 11 ኪሎ ግራም ክብደት የሚመዝን ድንች ተገኝቷል፡፡

ይህ ብዙም የተለመደ አይደለም የሚሉት አቶ አንሳር፣ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ክብደት ያለዉ ስኳር ድንች የተገኘዉ እስከ 3 ኪሎ ግራም የሚመዝን እንደነበር አንስተዋል፡፡

ይህ ከፍተኛ ክብደት ያለዉ የስኳር ድንች የተገኘዉ የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እህት ኩባንያ ከሆነዉ የቆቃ እርሻ ልማት መሆኑንም ሰምተናል፡፡

የእርሻ ማሳዉ በምስራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ ከአዲስ አበባ በ105 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ እንደሆነም አቶ አንሳር ነግረዉናል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply