12ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ ከዛሬ ግንቦት14 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል ተባለ፡፡ላለፉት 11 ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ሽልማትና እውቅና ሲሰጥ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/lS-uCFffAvyZsNXPXE4yOboIize5lpGwj-3en8TytniTtUnis3CgoGv6EDDjrX8xZbhbing6PX04WlkEgnJm_pgq2AZ1xfQYanZHsAM1nzmbFhPWZa6WK04UtjxfFychB7_JNiaXXVOYR-WkS_iepkBuD6X4J5w2bQun_KQv9Gw-H_rQusxceAMCUleFGA1vCrLhWTHcj8mu-huA5Z6LFFZfydFBxNh-nUDXbyuz6EIwV2rGV1tyDUzveeynKw5VTFEHa9gdk3zfp6k2484QhfyyxachAW-0DCocWsfAEIAQ69cz50jxbsCuixeqsKXSjGNmOCSDjPCl2D_EsepDFw.jpg

12ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ ከዛሬ ግንቦት14 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል ተባለ፡፡

ላለፉት 11 ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ሽልማትና እውቅና ሲሰጥ የቆየው የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅት ዘንድሮ ለ12ኛ ዙር ሽልማት፤ እጩዎችን ለመቀበል የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም ከዛሬ ግንቦት 14 እስከ ሰኔ 14/2016ዓ.ም ድርስ የእጩዎች ጥቆማ እንደሚከናወን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቋል።

የበጎ ሰው ሽልማት እውቅና ከሚሰጣቸው ዘርፎች መካከል መምህርነት፣ መንግስታዊ ኃላፊነት በአግባቡ የተወጡ አካላት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በጎ አድራጎት፣ ኪነጥበብ፣ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ተካተውበታል።

ከዚህ ባለፈ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሆነው በባህር ማዶ የሚኖሩ ለሀገር በጎ ተግባር ላበረከቱ ግለሰቦች ይሰጣል ተብሏል ።

በተገለፀው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ህዝቡ ለሽልማቶቹ ብቁ ናቸው የሚላቸውን አካላት በስልክ ቁጥር 09 77 232323 መምረጥ ይችላሉ ።
ከዚህ ባለፈ በፖስታ ቁጥር 150035 ላይ መልዕክት መላክ ይቻላል ተብሏል ።

#በልዑል ወልዴ
ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply