125ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ሲከበር የሚዘጉ መንገዶች ፡፡ 125ኛ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ነገ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ ፒያሳ በሚገኘው ምንሊክ አደባባይ…

125ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ሲከበር የሚዘጉ መንገዶች ፡፡

125ኛ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ነገ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ ፒያሳ በሚገኘው ምንሊክ አደባባይ እና በመስቀል አደባባይ በደማቅ ስነ-ስርዓት ይከበራል፡፡

አሽከርካሪዎች በዓሉ የሚከበርባቸው ቦታቸው አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

በዓሉ በልዩ ልዩ ፕሮግራምና በእግር ጉዞ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ይከበራል፡፡

በእለቱ መነሻውን ምኒሊክ አደባባይ የሚያደርገው ጉዙ በእሪ- በከንቱ ፣ በባሻ ወልዴ ችሎት ፣ በፓርላማ መብራት ፣ በአዋሬ ገበያ ፣ ሴቶች አደባባይ መድረሻውን አድዋ አደባባይ ይሆናል፡፡

በመሆኑም በዓሉን አስመልክቶ በምኒሊክ አደባባይ የሚካሄደው ፕሮግራም እስከሚጠናቀቅ

– ከደጎል አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደበባይ የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ

– ከራስ መኮንን ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ

– ከአፍንጮ በር ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር

– ከአዲሱ ገበያ ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሰሜን ሆቴል

– ከመርካቶ በአቡነጴጥሮስ ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን አደባባይ

-ከቸርችር ጎዳና ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ዝግ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ በመስቀል አደባባይ ለሚከናወነው ፕሮግራም
-ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር

-ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ቅዱስ ኡራኤል ቤተ- ክርስቲያን

– ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሄራዊ ቤተ-መንግስት መስቀለኛ

– ከቸርችር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ መብራት

– ከሚክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ለገሃር መብራት

– በሰንጋተራ ፣ በኮሜርስ ፣ በቴሌ ባር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኢትዩጵያ ንግድ ባንክ

-ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር ጋር ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን በዓሉ በሚከበርባቸው ቦታዎች ከማለዳው 11፡30 ሠዓት ጀምሮ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቋል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልፆ በዓሉን ለመታደም ወደ ዝግጀቱ ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ከበዓሉ ጋር ተፃራሪ የሆኑ መልዕክቶች ፣ ህጋዊ ከሆነው የፌደራል መንግስት እና የክልል መንግስታት ሰንደቅ ዓላማ ውጪ ይዞ መንቀሳቀስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል፡፡

ህብረተሰቡ ለጸጥታው አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ሲፈልግ በ011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply