125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በበይነ መረብ ውይይት ተከበረ

125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በበይነ መረብ ውይይት ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)125ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የአድዋ ድል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድልና ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ዓርማ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አክለውም ያለንበት ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የኢትዮጵያውያንን አንድነት የሚጠይቅ እንደሆነ ገልጸው፣ በመላ ኢትዮጵያውያን ቁጭት የተጀመረውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅና በሃገራችን ላይ እየተነዙ ያሉ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለመመከት ዳያስፖራው የቀደምት አባቶቹን አርአያ በመከተል በአንድነት ሊቆምና የራሱን ዳግማዊ የአድዋ ታሪክ ለመጻፍ ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ‘የአድዋ ድል፤ መንስኤ፣ ሂደትና ውጤት’ የሚል የውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡
በአውስትራሊያና ኒውዚላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመድረኩ ተሳትፈዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post 125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በበይነ መረብ ውይይት ተከበረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply