128ኛው የዓድዋ ድል መታሠቢያ በዓልን ለማክበር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ፍፁም ሠላማዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/YUTwcMqxNd0EbjHiCAcDi7MjfzLPxvYS7s7uGmmvI78iqJRsIENg7Q-swLJunQ8QZJvJJziAe984A-EbjER0GVpGrVVNdh848xsEd5Sgo8bsOSJe5-TgSQ00VEZA4f3Ms3K1ubhEUjpLbDsQtn75WNPL35Q_2jHWwiIZ2PKX4sN1-KSkxO-hIrlQ-BhMRYFDluXPnKGsw_iID4OQ3lKYykEQPwFAQB7NLBJ2n90EQEsCeOeTUxIG7wJZnpmPJkgT8CKSvMS9ZGgQSNc5KNAqtnEXzN6dBR5SSCl-p0BdlMU2UscO77RN4Mazm-gJ3Hs48FnKmXRpX-v98F4AETfN9A.jpg

128ኛው የዓድዋ ድል መታሠቢያ በዓልን ለማክበር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ፍፁም ሠላማዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደህነት የጋራ ግብረ ሃይሉ የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረው 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል በወጣው የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ውይይት አድርጓል።

የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻ ሃላፊ ጀነራል ተስፋዬ አያሌው በወቅቱ እንደገለፁት÷ የመላው ኢትዮጵያውያን በዓል የሆነው የዓድዋ ድል በዓል ሲከበር ምንም አይነት ስጋት እንዳያጋጥም የፀጥታ ሃይሉ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ÷ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን ሊያውኩ የሚችሉ ሁኔታዎች እንዳያጋጥሙ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማጥናትና በመለየት ችግሩን ለማስወገድና ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply