128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡ በዓሉ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡ ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ…

128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡ ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በስኬት እንዲከበር ለማስቻል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን ማስታወቁ ይታወቃል፡፡

ክብረ በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ
• ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ
• ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ
• ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ክብረ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግሙ በሚካሄድበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑንም ፖሊስ አሳስቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply