13 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጋር እየሰሩ አይደለም ተባለ፡፡ከ40 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ በሀገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ መስማማታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም…

13 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጋር እየሰሩ አይደለም ተባለ፡፡

ከ40 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ በሀገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ መስማማታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በሀገሪቱ በርከት ያሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸውን የሚያነሱት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሠ በርካታ የሀሳብ ልዩነቶች ሊኖር ስለሚችሉ የኮሚሽኑ አስፈላጊነቱ ላቅ ያለ ነው ብለውናል፡፡

በፖለቲካ ሂደቱ ዋነኛ ተዋናይ ከሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየሰራ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ወደ መድረኩ የሚቀላቀሉ ፓርቲዎች ቁጥር እጨመረ መምጣቱን ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከተመዘገቡ ከ40 በላይ ፓርቲዎች ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ 13 ከሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ምክንያቶች በምክክር ሂደቱ እየተሳተፉ አይደለም ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ወደ መድረኩ ያልመጡ ፓርቲዎች በርካቶች ነበሩ ያሉት ቃል አቀባዩ አሁንም 13ቱ ፓርቲዎችን በውይይት ለማሳተፍ እየተሞከረ ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ የተለያዩ ምክንያቶችን በማንሳት አንሳተፍም ያሉ ፓርቲዎችን በቅርበት በማነጋገር በጋራ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply