You are currently viewing 14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት በነፃ ዛሬ እንዲለቀቁ የባህርዳር ከፋተኛ ፍ/ቤት ወሰነ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል መስከረም 5 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ 14ቱ የአማራ ፋኖ አን…

14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት በነፃ ዛሬ እንዲለቀቁ የባህርዳር ከፋተኛ ፍ/ቤት ወሰነ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል መስከረም 5 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ 14ቱ የአማራ ፋኖ አን…

14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት በነፃ ዛሬ እንዲለቀቁ የባህርዳር ከፋተኛ ፍ/ቤት ወሰነ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል መስከረም 5 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ 14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት በነፃ ዛሬ እንዲለቀቁ የባህርዳር ከፋተኛ ፍ/ቤት ወሰነ። ለእያንዳንዳቸው 25 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከ50 ቀናት በፊት ከእስር እንዲፈቱ የባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ቤት መወሰኑ ይታወሳል።ይሁን እንጅ የባህርዳር ማረሚያ ቤት “ከላይ ታዝዠ ነው” በሚል ላለፋት 50 ተጨማሪ ቀናት አግቷቸው ቆይቷል። ይህን ተከትሎ ፋኖዎቹ በአካል ነፃ የመውጣት አቤቱታ ለባህርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሰሞኑን አቅርበው ሲከራከሩ ቆይተዋል።አቤቱታውን ተቀብሎ ያስተናገደው ከፍተኛ ፍ/ቤቱ 14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት እስካሁን ታግተው መቆየታቸው የፍ/ቤት ትዓዛዝን ባለማክበር እና በመናቅ መሆኑን ጠቅሶ ባስቸኳይ ዛሬ በነፃ ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል። አሁን በዚህ ሰዓት የባህርዳር ወጣቶች ጀግኖቻቸውን ሊቀበሉ ወደ ባህርዳር ማረሚያ ቤት እያቀኑ እንደሆነ በስልክ ገልፀውልኛል። አቀባበሉን እንደደረስኝ አቀርባለሁ ሲል ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply