You are currently viewing 140 ስደተኞች በሴኔጋል የባህር ዳርቻ ሰጠሙ

140 ስደተኞች በሴኔጋል የባህር ዳርቻ ሰጠሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 140 ስደተኞች በሴኔጋል የባህር ዳርቻ መስጠማቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ እንዳስታወቀው 200 ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በባህር ዳርቻው አቅራቢያ ሰጥማለች፡፡

ከአደጋው 60 ሰዎችን ማትረፍ መቻሉንም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ጀልባዋ መዳረሻዋን ወደ ስፔኗ ካናሪ ደሴት አድርጋ ትጓዝ እንደነበርም ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገልጿል፡፡

ተመድ አደጋው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየትኛውም የዓለም ክፍል በስደተኞች ላይ ከተከሰተው የከፋ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

The post 140 ስደተኞች በሴኔጋል የባህር ዳርቻ ሰጠሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply