15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከበረ ነው

15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና ሌሎች የመንግስት ስራ ሃላፊዎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ችቦን በጋራ በመያዝ በእግር ጉዞ በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡
የእግር ጉዞው ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በቸርችል ጎዳና እስከ ማዘጋጃ ቤት መሆኑ ታውቋል፡፡
በእግር ጉዞው ላይ ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በተጨማሪ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዓሉን ለመታደምም የተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ የመከላከያ ሰራዊቱ ድል ደስታ መግለጫ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም በድሉ የተሰማቸውን ደስታ እየገለጹ ሲሆን ÷የመከላከያ ሰራዊት ማርች ባንድ የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን እያሰማ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ተዘዋውሯል።
በምስክር ስናፍቅ

The post 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከበረ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply