15ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሐረሪ ክልል ተከበረ

15ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሐረሪ ክልል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 15ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሐረሪ ክልል ተከበረ።
በዓሉ “የህዝቦች እኩልነትና አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል መከበሩን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዝግጅቱ ላይ የአጎራባች ሶማሌ ክልል፣ የድሬዳዋ መስተዳድር እንግዶች እና የክልል የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተገኝተዋል።
በዓሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በህወሓት ጁንታ ላይ ድል በተቀዳጀበትና መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ደስታቸውን እየገለፁ ባሉበት ቀን ማግስት መከበሩ ድርብ ደስታ መፍጠሩንም ቢሮው አስታውቋል።

The post 15ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሐረሪ ክልል ተከበረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply