16ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በነገው እለት እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡ምክር ቤቱ ጉ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/aZeLwpxNB-D-nabFDRCHVu509RX6CM9vo8tKbmMDSC87nQfF4M5WK5Ad3UiwWjrb8RWc5FcLQsEf6u3HK1tW8Zp5iv-syt0zeqNkMw-6niWEVtE0-Z3kYuh5hajWYyd5311TGF565iSXSjDSktqIlHCYZv6hMOC19HF2BKWRYiHMziHkZ2uzXPHKJHuWTmvy1R8waOcf_Kkrw-mc6dPQTGfdKo2qkjEsFu-3ENyBMmq88M_Uh832dq3brnIlLWk5ivmsiJK44NwDU3pUjpAbZ8ncCwgF57pbrO8fgAfRhabIvtPKQNK553oIyOw9HQtiwpYede-d-A3WXq2W-O4aMw.jpg

16ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በነገው እለት እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ ጉባኤውን ከጠዋቱ ሶስት ስዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድም ተመላክቷል።

በዕለቱም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞች ሹመትን፣ የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እና የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን እና የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች እንደሚመራም ይጠበቃል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply