17ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሃዋሳ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀዋሳ እየተከበረ በሚገኘው 17ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/lh4R_EQ6TNUXJaWuF9bWqfiXYw9p92JMVZtqJtT-TWl6eReK3TXBBbqdCIa6SUz4sgAuoXuWPUhS3AoQ7Bm3gkZ4IS2t6gPBZQR-VTsiIWo7qUy07rctpAdoqfybSdtA7UjDQRUURYx4CqhKeuI-p4Dj9qf9LaP2stsNGcfVbgyzbmLztOrt8YK_qs6jZapvKeTSsCMV1TFyETwfHCeMam088yKs2F2o638HBdoQ0P2v_zeUMKzDgbj7vLPM3PwO7p8EF6ZkFPB9e_spgG0mBIuRFjGEZh0saZ4uBiJDAXFeLnv0bQFGlYHn54QdGUO661o_eTDJcVJbleLk-IOPYw.jpg

17ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሃዋሳ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀዋሳ እየተከበረ በሚገኘው 17ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክተ አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል፣ ኢትዮጵያ በድምቀት እና በሙላት የምትታይበት የኢትዮጵያዊነት ምልክት እና ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሁላችንም ቤት ናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በጋራ የምናድግበትንና የምንበለጽግበትን ሁኔታ በጋራ መፍጠር ካልቻልን ማናችንም በሰላም መኖር እና ወጥተን መግባት አንችልም ብለዋል፡፡

የእያንዳንዳችን ችግር ሊፈታ የሚችለው የሁላችንም ችግር ሲፈታ ነው፣ በተናጠል የራሱን ችግር ብቻ መፍታት የሚችል ማንኛውም ግለሰብ እና ቡድን ከኢትዮጵያ ችግር በፊት ቀድሞ የሚፈታ የሰፈር ችግር እንደሌለ መገንዘብ አለበት ነው ያሉት፡፡

እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ በዚህ ቀን የሁላችን ባህል፣ ታሪክ ቅርስ፣ እሴት፣ የኢትዮጵያ ሃብት እና የጋራ ኩራት ሆኖ የሚታይበት፣ ሁላችንም ለኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ መሆናችን እና ውበታችን በኢትዮጵያ ጥላ ስር ጎልቶ የሚታይ እና የምንማርበት ዕለት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው በሰሜን ኢትዮጵያ የጀመርነው ሰላም ዘላቂ አስተማማኝ እንዲሆን የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነውም ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply