17 ሺህ 200 ተማሪዎች ትምህርት የማቋረጥ አደጋ ላይ ናቸዉ ሲል የጃናሞራ ወረዳ አስተዳደር ገለጸ፡፡

በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ የሚገኙ 17 ሺህ 200 ተማሪዎች በክልሉ ባጋጠመዉ የከፋ ድርቅ ምክንያት ትምህርት የማቋረጥ አደጋ ላይ መሆናቸዉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ከጣብያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የጃናሞራ ወረዳ ምክትል አስተዳደር አቶ ሸጋዉ ተሰማ በወረዳዉ 38 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 2 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 17ሺህ 200 ተማሪዎች ተመዝግበዉ ትምህርት ቢጀምሩም የትምህርት ቁሳቁስና ምግብ እጥረት በማጋጠሙ ትምህርታቸዉን ሊያቋርጡ ይችላሉ ብለዋል።

በድርቅ ምክንያት በተከሰተዉ ረሀብ ምክንያት ትምህርት ሊያቋርጡ ይችላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች 16ሺህ 650 ተማሪዎች ትምህርታቸዉን መከታተል እንዳልቻሉም ተገልፃል።

በቅርቡ የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ባጠናዉ ጥናት ላይ በአማራ ክልል በከፋዉ ድርቅ ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸዉን መከታል እንደቸገራቸዉ ተገልጿል።

ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸዉ የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አምሳሉ ደረጄ “በተለይም ከቤተሰቦቻቸው ርቀዉ ትምህርት የሚከታተሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተቸግረዋል” ብለዋል።

ድርቁ በ100 የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ላሉ 54 ሺ 406 ተማሪዎች እንቅፋት ሆኗልም ተብሏል።

በአቤል ደጀኔ
ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply