179 ሰራተኞች እና 60 ተገልጋዮች በወንጀልና በሙስና ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደረገ፡፡የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ህገወጥ ተግባር ላይ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/eXXSuAtGhow2N3UiCfg9bs3vo3jO0BBaO5ND67vYA809raILYmt07MsiGvQUrxaUVcNhDv9sJEuARxY9-nAsfqpSUGbh5eIqBj5oFk3z26OrXpFDRRmzv57ETnfxxi4GJi__I3Eidy-qZVTcRbR7H_NZkgRxHyhULcEvWmpTfNm9fyCbgWMKbxDVr2ZdQYPj39gPedTQC_JJLekdbz3gVaRrRnZr9tL6Cki6RNDcsCdTmsX6PQGBbsvAMtK87Izz9hN7ZBkNBHCz8uxRts-FTxQbbTfRK2lcZ3q-Naw6pRsVziwg1Bc2fRKQEfAuqfaYNrXolGb3NJb92NeMfQsRvg.jpg

179 ሰራተኞች እና 60 ተገልጋዮች በወንጀልና በሙስና ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በተገኙ ሰራተኞቹና ተገልጋዮች ተጠያቂ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ዜጎች ከነዋሪነት መታወቂያ ጋር በተያያዘ ለእንግልት እና ለማጭበርበር የዳረጉ መስራቤቱ ሰራተኞች ተጠያቂ እንዳደረገ ነው ያስታወቀው፡፡

ሰራተኞቹ ተጣየቒ እንዲሆኑ የተደረጉት ያለ አግባብ መታወቂያ የሰጡ አገልግሎት ፈላጊውን ለእንግልት የዳረጉ እና ሙስና የተቀበሉ ናቸው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የነዋሪነት አገልግሎትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ተቋሙ ከ3ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት ተናግረው ሁሉም ሰራተኛ በህግ አግባብ ስራውን ይሰራል ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡

ከሰራተኞቹ በተጨማሪም ያለ አግባብ የልደት ሰርተፍኬት እንዲሁም የነዋሪነት እና የተለያዩ ሰነዶችን ያዘጋጁ ተገልጋዮችም እንዲቀጡ መደረጉን ዳሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን ማግኝት በማሰብ ዜጎች ከሚገኙባቸው አካባቢዎች መታወቂያ ለማግኝት አስፈላጊውን መረጃ ይዘው ቢገኙም በህግ አግባብ እየተስተናገዱ እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት፡፡

ዜጎች በህጉ መሰረት መታወቂያ እንዳያገኙ ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል በመስራቤቱ ያሉ ሌቦች በሚፈጥሩት ጫና ነው ያሉት ሃላፊው ይህንን መታገል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከነዋሪነት መታወቂያ እና ከሌሎችም አገልግሎቶች ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ መስራቤቱ አዲስ አሰራር ለመተግበር ዝግጅት ማድረጉን አቶ ዮሴፍ ነግረውናል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply