207 ንጹሃን ዛሬ በቡለን ወረዳ ቀብራቸው በጫካ ተፈፀመ፡፡              አሻራ ሚዲያ      ታህሳስ፡-16/04/ 2013 ዓ.ም ባህርዳር በቡለን ወረዳ…

207 ንጹሃን ዛሬ በቡለን ወረዳ ቀብራቸው በጫካ ተፈፀመ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-16/04/ 2013 ዓ.ም ባህርዳር በቡለን ወረዳ…

207 ንጹሃን ዛሬ በቡለን ወረዳ ቀብራቸው በጫካ ተፈፀመ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-16/04/ 2013 ዓ.ም ባህርዳር በቡለን ወረዳ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት 207 ንጹሀን ዛሬ 6 :00 ሰዓት አካባቢ በጅምላ ተቀብረዋል፡፡ የቡለን ወረዳ ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው በታጣቂዎች የተገደሉ 207 ሰዎች በጅምላ በጫካ የተቀበሩት የተለያየ ሀይማኖት በመሆናቸው ነው ብሏል፡፡ ነገር ግን በየሀይማኖት ስራዓታቸው አለመቀበራቸው ኮማንድ ፓስቱን ለትችት እየዳረገው መሆኑንም ገልጻል፡፡ የቡለን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅህፈትቤት እንደዘገበው መከላከያው ወደ አካባቢው ቀብር ለመፈፀም ገብቷል፡፡ መከላከያው ቀብር ለመፈፀም እንጂ ለማዳን አለመድረሱ ትዝብት ውስጥ ከቶታል ነው ያለው በመግለጫው፡፡ ዛሬም የመከላከያ አመራሮች ጀኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ በመተከል ቢገኙም በህዝቡ ዘንድ አመኔታ አላገኙም፡፡ በመከላከያ የበላይ አመራር ባሉ ፖለቲከኞች ምክንያት የእዝ ሰንሰለቱ ውጤታማ ስራ ለመከወን ተስኖታል ነው የተባለው፡፡ ሶስት ወር መተከልን እንዲመራ መከላከያው ትዕዛዝ ቢሰጠውም ሞት እና መፈናቀልን ማዳን አልቻለም፡፡ የብልጽግና ፖለቲካ ብልሽት ለመከላከያው ድክመት መንስኤ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply