22 ሽ የአማራ ተማሪዎች ወደትምህርታቸው ሊመለሱ ነው የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 29 2013 አ/ም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ሲታገልባቸው  ከቆየባቸው ጥያቄዎቹ መካከል ተፈናቃይ…

22 ሽ የአማራ ተማሪዎች ወደትምህርታቸው ሊመለሱ ነው የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 29 2013 አ/ም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ሲታገልባቸው ከቆየባቸው ጥያቄዎቹ መካከል ተፈናቃይ…

22 ሽ የአማራ ተማሪዎች ወደትምህርታቸው ሊመለሱ ነው የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 29 2013 አ/ም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ሲታገልባቸው ከቆየባቸው ጥያቄዎቹ መካከል ተፈናቃይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚል ነበር። ከ22ሺህ በላይ የሚሆኑ የአማራ ተማሪዎች በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጸጥታ ችግር ምክኒያት ከትምህርታቸው ተፈናቅለው ቆይተዋል ማህበራችንም በተከታታይ ከመንግስት ጋር ውይይቶችን በማድረግ ጥያቄዎቹን ሲያቀርብ ቆይቷል። በመጨረሻም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምኒስቴር ጥያቄያችንን ተቀብሎ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተነሱ ግጭቶች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የተገደዱ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ውሳኔ አሳልፏል። ለተመለሰው ጥያቄ እና ትልቅ ተሳትፎ ለነበራችሁ አጋር አካላት ምስጋና እያቀረብን ሌሎች ጥያቄዎቻችንም በተመሳሳይ መልኩ ምላሽ እንዲያገኙ ጥሪያችንንም ትግላችንንም አጠናክረን እንቀጥላለን ሲል የዘገበው አተማ በማህበራዊ ድህረገጹ ነው::

Source: Link to the Post

Leave a Reply