23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ሊገነቡ ነው፡፡ከፍተኛ የአውሮፕላን ማረፍያ በሌለባቸው ነገር ግን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አሉባቸው በሚባልባቸው አካባቢዎች ትናንሽ አየር ማረፍያዎች እንደሚ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/EvksmpXsSpFZo_b0SrmeSSwK2MgWjG7i3PvyvhnpN4mxBVHaJ_kjFXVNwZcfRKwbtxp5PX4QWy4D7J-V7Jpq8zfxDeoLoAfVrYkB8sg3Dc7HwpnFCSgVrAE6IQjha30Ep11aB8FWLjZDjx78gWorlySZPv5hwoti4BMzxdJl5L4aSlRkPQyGWJa69UuoxQbZe5h26oVvao6H6udKRQG7dKoDPRprMt7bthY4TR1AeKUY1oclBLzPNxaPK7GgTLvp_U2XzQ53cDokMIeDTzfxLBn-H7KM5Koo1lqm--9RPYrAUANOV8sNqkgTUaWRrLxdk4fHPA4YAzGDoXh23jbPTQ.jpg

23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ሊገነቡ ነው፡፡

ከፍተኛ የአውሮፕላን ማረፍያ በሌለባቸው ነገር ግን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አሉባቸው በሚባልባቸው አካባቢዎች ትናንሽ አየር ማረፍያዎች እንደሚገነቡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስትክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ የኢትዮጵያ መንግስት ለአዳዲስ የአውሮፕላን ማረፍያዎች ግንባታ የሚሆን በጀት አለመያዙን ተናግረው አሁን የሚገነቡ ትናንሽ አየር ማረፍያዎች በተለያዩ ወጪዎች የሚሸፈኑ ይሆናል ብለዋል፡፡

በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የሚገነቡት 23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ተለይተው መታወቃቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ የአዋጭነት ጥናት የመሬት ጥናት እና ሌሎችም ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

እነዚህ ግንባታዎች በራሳቸው ወጪ ለማከናወን የክልል መንግስታት ፍላጎት ማሳየታቸው የተነገረ ሲሆን ባለሃብቶችም ጭምር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተነገረው፡፡

በሔኖክ ወ/ገርብርኤል

ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply