24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ

24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦነግ ሸኔ የአጥፊ ቡድን ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን እና በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
ሰሞኑን የኦነግ ሸኔ ቡድን በፈጠረው የሽብር ተግባር የዜጎች ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ይህን እኩይ ተግባር በፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።
በዚህም በተለይ በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭቃኔ የተሞላበት በኦነግ ሸኔና በህወሃት ደጋፊነት የተወሰደው እርምጃ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ይታወቃል ብለዋል።
የክልሉ ፖሊስ ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ ባደረገው ክትትል በተለያዩ አቅጣጫዎች በምዕራብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኦሮሚያ በአጠቃለይ በኦነግ ሸኔ ላይ
በተደረገ ክትትልና በተወሰደው እርምጃ እስካሁን 24 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

The post 24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply