25% እንዲያገኝ ይደረጋል!ሀብት ያላስመዘገቡ አመራሮችንና ባለሙያዎችን የጠቆመ ሰዉ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ ይደረጋል—-የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽንሀብት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/guJG1gsHd8ukMiFj0u5f9Oa7GxLPb5KGUIvF4SpL_Wfc0faNlu6NmzLV3w2kKfuNAXyCwY1KsiOfo6KWtCapbHJL1-JIiq3rhjP7OwvDOKPskNe4rZRnL4IHoBPCWhhsN2Wo4bEOErmJMtP5AFWPv5i0_xzuWt_X8ntuHg6cfGOoL962tJcQc51UhzuJMQir6LksElb67NWIXCCSO1KD9UXAKhYdahv4a0hgcRMkZG6trdwz3cASp8edmnSU1d7J8nM0cbq6wHIv-E8Fmt9iSz8S3QcJWgHU45OcT7Dep_0Y2F5wPClJIWEf52fgb1O2_Po6128HqyXkJE7Cd2RHHg.jpg

25% እንዲያገኝ ይደረጋል!

ሀብት ያላስመዘገቡ አመራሮችንና ባለሙያዎችን የጠቆመ ሰዉ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ ይደረጋል—-የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

ሀብት በማስመዝገብና በማሳወቅ ሂደት፤ አመራሮችንና ባለሙያዎች ሳያስመዘገቡ የቀሩትን ሀብት የጠቆመ ዜጋ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ እንደሚደረግ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።

ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ በፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስ እና መረጃ አስተዳደሥ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፈርዳ ገመዳ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም በአዋጅ ቁጥር 668/2002 በግልፅ መስፈሩን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን 763 የመንግስት አመራሮችን ቢለይም፤ እስካሁን ሀብታቸውን ያስመዘገቡት 20 በመቶው ብቻ መሆናቸው ተጠቅሷል።

እስካሁንም 2 ሺሕ 272 የፌደራል ተቋማት መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ሀብታቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ሰዎች በህግ ፊት ተጠያቂ ከመሆናቸው በፊት እንዲያስመዘግቡም ጥሪውን አቅርቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም107. የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply