273 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

273 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስር ቤት የነበሩ 273 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ከሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ከተማ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በጄዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ከዛሬ ተመላሾች ውስጥ 134 ታዳጊ ልጆች፣ 137 ሴቶች እና 2 ህጻናት መሆናቸውን ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሳዑዲና የሀገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተደረገው ጥረት ጄዳ ከተማ ከሚገኘው የሼሜሲ እስር ቤት ወተው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ነው የተነገረው።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ጉዳዩ ከሚመከታቸው መስሪያ ቤቶች የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከጄዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

The post 273 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply