28 ሺ ስራ አጦች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ ሊሰማሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው በወጣቱ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ውይይት ከሁለት ሳምንት በፊት በከተማ ደረጃ ማካሄዱን መግለጹ ይታወሳል፡፡አንድ ሺ ገደማ ወጣቶችን ያሳተፈው ውይይት በክፍለ ከተሞች ደረጃም እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ማስተባበሪያ ቢሮው በመዲናዋ ለሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በዚህም በቅርቡ ለሃያ ስምንት ሺ  የመዲናዋ ስራ አጦች የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አሰጥቶ ማስመረቁን አስታውሷል፡፡

ከነዚህ መካከል 95 በመቶዎቹ ወጣቶች መሆናቸውን የገለጹት አቶ ጥበቡ፣ ተመራቂዎቹ በየመረጡት ዘርፍ ለመሰማራት ልየታው ተጠናቆ እየተደራጁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ሰልጣኞቹ የወንዝ ዳርቻዎችን ማልማት፣ በከተማ ውበት መጠበቅ፣አደባባይ ማልማት፣ በንብ ማነብና ችግኞችን በመንከባከብ ዘርፍ እንደሚሰማሩ የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ጥበቡ በቀለ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ቀን 14/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post 28 ሺ ስራ አጦች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ ሊሰማሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply