3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ተመርቶ ለህብረተሰቡ በነፃ ሊሰራጭ ነው

3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ተመርቶ ለህብረተሰቡ በነፃ ሊሰራጭ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ተመርቶ ለህብረተሰቡ በነፃ እንደሚሰራጭ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የአግሮ ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዮቲካል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረእየሱስ እንደገለፁት ከጅ አይ ዜድ በተገኘ ድጋፍ በተመረጡ 36 የጨርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች ተቀጥረው ለሚሰሩ 12 ሺህ ሰራተኞች የሁለት ወር ደመወዝ ይከፈላል ብለዋል፡፡

ሰራተኞቹ ተቀጥረው በሚሰሩበት ፋብሪካ በወር ውስጥ 150 የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማምረት እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ተመርቶ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በነፃ እንደሚሰራጭ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው አክለውም ዘርፉን ለማሳደግ መንግስትና የልማት አጋሮች ከሚያደርጉት ድጋፍ በበለጠ የዘፉር ባለቤቶች ከከፍተኛ እስከ አነስተኛ አምራቾች በትስስርና በጋራ ሰርቶ የመበልፀግ እሳቤ መስራት እንደሚያስፈልግ መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የጨርቃጨርቅና ቆዳ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አበበ በበኩላቸው ጂ አይ ዜድ ያደረገውን ድጋፍ ውጤታማ በመሆነ መልኩ ለመተግበር የስልጠና፣ የክትትልና ድጋፍ ማኑዋል የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀው ዘርፉን ለማሳደግና የተሻለ ለውጥ ለማምጣት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

 

 

The post 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ተመርቶ ለህብረተሰቡ በነፃ ሊሰራጭ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply