30 ደላሎች በህግ እንዲጠየቁ ተደረገ፡፡

በባለፉት ጊዜያት ከፓስፖርት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ደላሎች የፈጠሩት አሉታዊ ጫኛ ከፍተኛ እንደነበረም ነው የተገለጸው፡፡

ከፓስፖርት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ከውጥ ሰራተኞች ጋር በመቀናጀት በህገወጥ ስራ ላይ የነበሩ ደላሎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተነግሯል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ደላሎች ከኢሚግሬሽን ሰራተኞች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውን የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በዚህም መረጃ የተገኘባቸውን ለህግ አካላት የማቅረብና እንደየጥፋታቸው በህግ እንዲጠየቁ እንደተደረገም ነው የተገለጸው፡፡

ተቋሙ በባለፉት 9ወራቶች በሰራው የሪፎርም ስራ የተቋሙን አሰራር የጣሱ ከፍተኛ አመራሮች ተጠያቂ የማድረግ፣ የስነምግባር ጉለት የተገኝባቸው ሰራተኞች አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው እና ለበርካታ ዜጎች አዲስ ፓስፖርት የመስጠትና የማደስ ስራ መስራቱን አስታውቋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply