37ኛውን የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነውጉባዔውን ለመዘገብ ከመላው ዓለም ከ500 በላይ ጋዜጠኞች ይገኛሉ ተብሏል።በመጭው ቅዳሜ እና እሁድ…

37ኛውን የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

ጉባዔውን ለመዘገብ ከመላው ዓለም ከ500 በላይ ጋዜጠኞች ይገኛሉ ተብሏል።

በመጭው ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

ከነዚህም መካከል ዛሬ ጠዋት የገቡት የጊኒው ቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሴኮ ኢምባሉ፣ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና የኬፕ ቨርዲ ፕሬዚዳንት ጆሴ ፔረራ ነቪስ ፤ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ይገኙበታል፡፡

የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫም ትላንት ማምሻውን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ መሪዎች የተለያዩ የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውንም የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አመልክተዋል።

ውይይቱም በቅርቡ የብሪክስ አባል የሆነችው ኢትዮጵያ ከነባር የብሪክስ አባሏ ብራዚል ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር አንድ እርምጃ ነው ተብሏል።

የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ዛሬ ጠዋት የአድዋ ድል ሀውልትን ከባለቤታቸው ጋር ሲጎበኙ ታይተዋል።

በጎርጎሪያኑ የካቲት 17 እና 18 ቀን 2024 ዓ/ም በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ 49 ሀገራት ተወካዮች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የ13 ዓለም አቀፍ ተቋማት እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ አስታውቋል።.

ጉባዔውን ለመዘገብ ከመላው ዓለም ከ500 በላይ ጋዜጠኞች አዲስ አበባ መግባት መጀመራቸውንም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ድኤታ ላማዊት ተናግረዋል።

የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply