4ኛው ዙር የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የሀገራችን ክልል ከተሞች  ተከበረ

4ኛው ዙር የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የሀገራችን ክልል ከተሞች ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)4ኛው ዙር የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የሀገራችን ክልል ከተሞች ተከብሯል።

በአዲስ አበባ ከቤቴል እስከ አንፎ አደባባይ መንገድ ላይ በተለያዩ ሁነቶችና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፣ የእግርና የብስክሌት ጉዞ እንዲሁም በመከላከያ ማርች ባንድ ታጅቦ ሲከበር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አወል ወግሪስ ናቸዉ።

በመልዕክታቸውም የትራፊክ አደጋ ችግር አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት እና የብስክሌት ትራንስፖርትን ለማበረታታት “ከጳጕሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን!” በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረውን ንቅናቄ ተጠናከሮ ቀጥሎ ለ4ተኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ መሆኑን አንስተዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ከአለም አቀፍ አማካሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀ እና ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን በስትራቴጂው የእግር ጉዞ፣ የሳይክል ትራንስፖርት እና በካይ ያልሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አማራጮችን መጠቀምን ያበረታታል መባሉን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post 4ኛው ዙር የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የሀገራችን ክልል ከተሞች ተከበረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply