
<<..ኦነግ አዲስ አበባ ተቀምጦ "እኛ በአማራነታችን አዲስ አበባ ፖሊስ ታስረናል በጣም ያሳፍራል‼[ጋዜጠኛ ገነት አስማማው] ክፍል ሁለት ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ <<..እኔ በስራዬ ጋዜጠኛ ነኝ ማንነቴ ከጠየከኝ አማራ ነኝ ይኽንን መለውጥ አልችልም።" በአማራነቴ ለማሸማቀቅ ሲፈልጉ እኔ እኮራበታለሁ የጠሉት ሙያዬን ሳይሆን ማንነቴን ነው ለዛ ደግሞ በርካታ በደሎች ደርሶብኛል። ስያዝ ተደብዴቤአለሁ የስነልቦና ጫና አድርሰውብኛል። <<..ኦነግ አዲስ አበባ ተቀምጦ "እኛ በአማራነታችን አዲስ አበባ ፖሊስ ታስረናል በጣም ያሳፍራል። የብልፅግና መሪ ዐቢይ አህመድ የአማራ ህዝብ በተፈጸመበት ጄኖሳይድ መጠየቅ አለበት በርካታ በደሎች በዚህ አምስት አመት ተፈጽሟል ባለቤቱ ዐቢይ አህመድ ነው። ጋዜጠኛ ሆኜ ይህን መዘገብ ግዴታዬ ነው ክሳችን ለምን ወንጀላችን አጋለጣችሁ ነው። ለምን ዘገባችሁ ተብሎ ነው ስራዬ እንደ ጋዜጠኛ ለተጎዳው ህዝብ ሽፋን መስጠት ሙያዊ ግዴታዬ ነው የታሰርኩት ግን እንደ አማራ ነው። ትልቅ በደል ተፈጽሞብናል። "በእስሬ እናቴ በጣም ትጨነቃለች ይኽን ስራ ለምን አትተይም ትለኝ ነበር አሁንም ድረስ እንደጥፋተኛ በመቁጠር ቀድሜ ነግሬሽ ነበር በማለት ትናገረኛለች እኔ ብተዋቸው ማንነቴን አይተውትም ስላት መልሳ ታበረታኛለች። አሁን እየገባት መጥቷል አልሰበረም! ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ከስንታየሁ ቸኮል "ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።" ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post