455 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 845 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

455 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 845 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታትለ 6 ሺህ 28 ሰዎ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 455 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 99 ሺህ 201 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 845 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎም 58 ሺህ 948 ሰዎች ከቫይረሱ እስካሁን አገግመዋል።

በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ እስካሁንም 1 ሺህ 518 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 733 ሰዎች መካከል 306 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

The post 455 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 845 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply